2010-06-28 13:20:50

ቅድስት ሥላሴ፣ የሁሉም ፍቅር መሠረት አርአያ እና ፍጻሜ


የቲዮሎግያ እና የፍልስፍና ሊቅ ፈረንሳዊ ካህን ኣባ ረነ ላውረንቲን፣ ቅድስት ሥላሴ የሁሉም ፍቅር መሠረት አርአያ እና ፍጻሜ በሚል ርእስ ሥር የስነ ቅድስት ሥላሴ ቲዮሎጊያዊ ትንታኔ አዘል ዓቢይ መጽሓፍ ለሕትመት RealAudioMP3 ማብቃታቸው ተገልጠዋል።

ኣባ ረነ ላውረንቲን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅድስት ሥላሴ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ግልጸት መሠረት የተደረሰው ግንዛቤ የሁለት ሺሕ ዓመት ዕድሜ ያለው የሥነ አንቀጸ ሃይማኖት ቲዮሎጊያ በመተንተን፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አብነት በመከተል የቅድስት ሥላሴ ምሥጢር ለመኖር እንደሚቻልም ያስተምረናል ብለዋል። ቅድስት ሥላሴ እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑ የሚያረጋገጥልን ምሥጢር ነው፣ ሁሉም ይኸንን ፍቅር እንዲኖሩ እና እርስ በእርስ በመፋቀር እንዲኖሩ ሁሉም በፍቅር መሠረት አንድ-ነቱን ያረጋግጥ ዘንድ የሚያስገንዘብ የፍቅር ምሥጢር ነው፣ ሶስት ሰዎች በፍቅር አንድ ይሆናሉ።

ቅድስት ሥላሴ እግዚአብሔር ነው፣ ይህ ደግሞ አንድ እና ሦስትም ነው፣ አንድ ነው ምክንያቱም ጣኦቶች ኣይደለምና፣ ሦስትም ነው ምክንያቱም ሦስት አካል ነውና፣ የአካል ሦስትነት ከሌለ ፍቅር አይኖርም፣ ስለዚህ በሦስቱ አካል ያለው የፍቅር መግለጫ ነው። ሦስቱ አካላት በመሠረቱ አንድ-በአንድ-ነት ይኖራሉ፣ በዚህ አንድ-ነት ልዩ የሆነውን የእግዚአብሔር ቀዋሚ ነገርን ይኖራሉ፣ ካሉ በኋላ በደረሱት መጽሓፍ፣ ለእኛ ለአማኞች በእምነት እና በምርምር መካከል ያለው ግኑኝነት፣ የተሟይነቱ ሂደቱን በማብራራት፣ በ 1900 ዓመታት ምርምር ብቻ ሁሉም የሚገልጥ ሁሉን የሚያስረዳ እና ምርምር የማይተነተነው እና የማይደርስበት ሁሉ የሌለ እንደሆነ የሚገልጡ ብዙ መላ ምቶች የቀረበበት ዘመን እንደነበር ገልጠው፣ እለታዊ የሕይወት ገጠመኝ ምርምር የማይደርስበት የማይገልጠው እውነት እንዳለ ይጠቁማል። ቅድስት ሥላሴ በሥነ ምርምር የሚደረስ የሚጨበጥ አይደለም ቢሆንም ግን ማስረዳቱ ማስተማሩ እና እምነትነቱን መግለጥ የሚቻል ነው ስለዚህ የደረሱት መጽሓፍ ይኽንን የሚዳስስ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.