2010-06-28 13:17:20

ቅ.አ. ር.ሊ.ጳ. ለቤልጂም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መልእክት አስተላለፉ


ባለፈው ዓርብ በበልጂም የማሊነስ እና ብራሰልስ ካቴድራል የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወርሃዊ ስብሰባ እያካሄድ በነበረበት ወቅት የብራሰልስ የበላይ ፍርድ ቤት መርማሪ ቡድን በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት RealAudioMP3 የተፈጸመው የወሲብ አመጽ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መረጃ ለማሰባሰብ በሚል ውሳኔ መሠረት ዘልቀው በመግባት በቤተ ክርስትያን ሥር የሚገኘው የመቃብር ሥፍራ ድረስ በመሄድ ያካሄዱት ፍተሻ እና ብፁዓን ጳጳሳቱን እዛው በማገት በበልጂም ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ድረስ ለረዥም ሰዓታት ያካሄዱት ፍተሻ እና የቃል ምርመራ ተግባር በማስመልከት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለማሊነስ እና ብራሰልስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ አንድረ ጆሴፍ ለኦናርድ ባስተላለፉት መልእክት የመርማሪው ቡድን የፈጸመው የፍተሻ ተግባር የሚያሳዝን እና የሚያስቆጣ መሆኑ በመጥቀስ፣ ሙሉ ትብብራቸውን እና ቅርበታቸውንም ለሰበካው ለብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ለዮናርድ ለመላ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት በበልጂም ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ባስተላለፉት መልእክት አረጋገጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባስተላለፉት መልእክት፣ በውሉደ ክህነት አባላት የተፈጸመው እና ተፈጽምዋል የሚባለው የወሲብ አመጽ ጉዳይ፣ የቤተ ክርስያን ሕገ ቀኖና እና ወንጀሉ በተፈጸመበት አገር ባለው ሕግ መሠረት እንዲታይ ውሳኔ ማስተላለፋቸው በማስታወስም፣ ጉዳዩን የሚያጣሩ ፍርድ ቤቶች አለ ምንም ጅምላዊ ቅድመ ፍርድ የሰዎችን እና የመዋቅሮች በተለይ ደግሞ የወሲብ አመጽ ሰለባ የሆኑትን ሰዎች መብት እና ግዴታን በማክበር በቅንነት የምርመራ ሥራቸውን ያከናውኑ ዘንድ አደራ እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.