2010-06-26 13:17:43

የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ


ሮኣኮ በመባል የሚጠራው የተለያዩ የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የሚደግፍ የግብረ ሰናይ ማኅበር 83ኛው ጉባኤ እ.ኤ.አ. የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን ጉዳይ የሚከታተል ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ በመሩት RealAudioMP3 መሥዋዕተ ቅዳሴ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፣

በዚህ የተራድኦ ተግባር ለምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የተሰኘው ማኅበር 83ኛው ጠቅላይ ጉባኤ ንግግር በማሰማት ስብሰባውን ያስጀመሩት ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ፣ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና ባለፈው ሳምንት የተገባደደው የክህነት ዓመት አቢይ ግምት እንዲሰጠው በማሳሰብ፣ መካከለኛው ምሥራቅ የአስፍሆተ ወንጌል ጅማሬ መሆኑንም አስታውሰው፣ የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በዚህ ክልል አስፍሆተ ወንጌል ዳግም በአዲስ መንፈስ ለማነቃቃት የሚደግፍ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጠው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የማኅበረ ክርስትያን ብዛት መጓደል እና ከቀን ወደ ቀን ወደ ስደት የማዝገሙ ጉዳይ ክልሉ አለ ማኅበረ ክርስትያን ይቀራል የሚለው እጅግ አሳሳቢ እየሆነ ያለው ማኅበራዊ ጉዳይ በጥልቀት በማብራራት፣ ጉዳዩ መፍትሔ እንዲያገኝ የዚህ የተራድኦ ተግባር ለምሥራቅ አቢያተ ክርስያን ማኅበር የሚሰጠው ድጋፍ እና የሚገልጠው ቅርበት አቢይ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

በመቀጠል ንግግር ያሰሙት በቆጵሮስ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዩሰፍ ሱዌፍ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የማኅበረ ክርስትያን ጠቅላይ አድማስ ርእስ በማድረግ ንግግር በማሰማት፣ የክልሉ ፖለቲካዊ ችግር በማኅበረ ክርስትያንም ይሁን በጠቅላላ በክልሉ ሕዝብ ላይ አቢይ ትጽእኖ እንዳለው አብራርተው፣ ስለዚህ በዚህ ዘርፈ ብዙ ችግር በሚፈራረቅበት ክልል የበለጠውን ዓለም ለመገንባት የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ኅላዌ እጅግ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ክልል የሚሰጠው ድጋፍ ክልሉ አለ ክርስትያን እንዳይቀር ያለመ ሳይሆን፣ በክልሉ ኅብረአዊነት እና በውይይት የሚገለጠው የፍቅር ባህል ለማዳን የጨመተ መሆን አለበት፣ ምክንያቱ የፍቅር ባህል በማዳን ብቻ ነው ሁሉም በመረጋጋት ለመኖር የሚችለው ብለዋል።

በመቀጠል የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲኮቶስ 16ኛ በቆጥሮስን ሓዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ለመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ያቀረቡት ለመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሥራ ማካሄጃ ሰነድ ላይ ያተኮረ ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ ተግባእያኑ ትላንትና ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር በመገናኘት እና መሪ ቃል በመቀበል ስብሰባውቸውን እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.