2010-06-26 13:15:53

እሴቶች እና የሰብአዊ መብት እና ግዴታ


የኤውሮጳ ህብረት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ፍርድ ቤት በኢጣሊያ ትምህርት ቤቶች የክርስትና የላቀው የእምነት ምልክት የሆነው መስቀል እንዳይሰቀል እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ያስተላለፈው የመጀመሪያው ውሳኔ፣ RealAudioMP3 ፍርድ ቤቱ የኢጣሊያ የይግባኝ ጥያቄ እና 10 የህብረቱ አባል አገሮች ኢጣሊያን በመደገፍ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በመቃወም የሰጡት መግለጫ መሠረት፣ እ.ኤ.አ. ሰነ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ዳግም ውሳኔ ሊሰጥበት መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት፣ የኢጣሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና የኢጣሊያው ክርስትያናዊ ሰብአዊነት እንቅስቃሴ በመተባበር እሴቶች እና የሰብአዊ መብት እና ግዴታ በሚል ርእስ ሥር ያነቃቁት ዓውደ ጥናት በሮማ የባህል ጉዳይ ምክር ቤት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ ሲገለጥ፣ የኢጣሊያ ርእሰ ብሄር ጆርጅ ናፖሊታኖ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ እና የኢጣሊያ መራሄ መንግሥት ሲልቪዮ በርሉስኮኒ ለጉባኤው መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ባስተላለፉት መልእክት ኤውሮጳ ከማንኛውም ዓይነት እምነት ነጻ የሆነው የምትከተለው የዓለማዊነት አመለካከት ሕዝባዊ እና ጥልቅ ስሜቶች የሚጎዳ ሆኖ መገኘት የለበትም ብለዋል። በዚህ ዓውደ ጥናት የኢጣሊያ የባህል ጉዳይ ሚኒ. ሳንድሮ ቦንዲ፣ የሰራተኛ እና የማኅበራዊ ፖሊቲካ ጉዳይ ሚኒ. ማውሪዚዮ ሳኮኒ፣ የቅድስቲ መንበር የሕጎች ሰነዳት ተንታኝ ምክር ቤት ሊቀ መንበር የነበሩት የሕግ ሊቅ ብፁዕ ካርዲናል ኹሊያን ሄራንዝ በመሳተፍ ንግግር ማሰማታቸው ለማወቅ ተችለዋል።

የኢጣልያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ባስተላለፉት መልእክት የኤውሮጳ ህብረት አገሮች ሃይማኖታዊ መለያ እና ምልክት የእያንዳንዱ አባል አገር የሉኣላዊነት ውሳኔ እንጂ የህብረቱ የበላይ ፍርድ ቤት የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፣ ስለዚህ የስቁል ኢየሱስ ቅዱስ ምስል ለሃይማኖታውያን እሴቶችን ብቻ ሳይሆን ለሥልጣኔም ጭምር መሠረት መሆኑ አብራርተዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ባስተላለፉት መልእክት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ ምስል ቅዱስ መስቀል፣ ከኢጣሊያ እንዲሁም ከኤውሮጳ የሃይማኖታዊ ስሜት ታሪክ እና ባህል ጋር በጥብቅ የተቆራኘ የማንነት መለያ እና መግለጫ መሆኑ ማብራራታቸው ሲገለጥ፣ የቤተ ር.ሊ.ጳ. ምስለኔ ብፁዕ አቡነ ፓውሎ ደ ኒኮሎ በተካሄደው ዓውደ ጥናት ባሰሙት ንግግር፣ የስቁል ኢየሱስ ቅዱሱ ምስል የኢጣሊያ ጥልቅ እና እጅግ አስፈላጊ የሃይማኖት መሠረተ ነገር እና መሠረተ ሓሳብ ነው፣ ለኢጣሊያ ብቻ ሳይሆንም ክርስትያናዊ መሠረት ላለው ለምዕራብም ይሁን ለምሥራቁ ዓለም ባህል የመሠረት ድንጋይ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅርቡ ቆጵሮስን በመጎብኘት፣ ቢኒቆስያ በሚገኘው የቅዱስ መስቀል ቤተ ክርስትያን መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው ባሰሙት ስብከት ለአማኙ መስቀል ከባህላዊ እውነተኛ ጉዳይነቱ የላቀ ትርጉም ያለው ነው በማለት፣ መስቀል በብቃት በሙላት በጥልቀት የሚናገር ነው እና በሥሩ ተንበርክከን የሚለንን እናዳምጥ ማለታቸው ብፁዕ አቡነ ኒኮሎ አስታውሰዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ኹሊኢያን ሄራንዝ ባሰሙት ንግግር፣ በአሁኑ ወቅት ከአወንታዊው የዓለማዊነት ርእዮት የመነጨ የዓለማዊነት ርእዮት አክራሪነት ሁሉም የሚቀበለው እና የሚታዘዘው ሕግ ለመሆን እየቃጣው ነው፣ በሌላ አነጋገር ይላሉ የዓለማዊነት ርእዮት አክራሪነት ለገዛ ራሱ ልክ ሃይማኖት እየሆነ ነው፣ የሕግ ሊቃውንት የቤተ ክርስትያን አካላት የቅዱስ መስቀል ቅዱስ ምስል፣ የአንድ መንግሥት ዓለማዊነት ለአደጋ አያጋልጥም፣ ምክንያት ክርስቶስ የቄሳር ለቄሳር የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር በማለት አስተምሮናል፣ ስለዚህ ቅዱስ መስቀል እጅግ በበለጠ የሃይማኖት ምልክት ከመሆኑ በፊት የሰብአዊ እሴቶች ምልክት ነው እንዳሉ ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚሰጠው ውሳኔ በባህላዊ አመለካከት መንግሥታት የኅብረትሰብ አገግልጋዮች ናቸው፣ እንዲሁም የኤውሮጳ ህብረት የኤውሮጳ ኅብረተሰብ አገልጋይ ነው፣ ስለዚህ አገልግሎቱ በኅብረሰብ ላይ እንደ ርእዮት ዓለም፣ ባስገዳጅነት ለማሰራጨት መጠመድ ማለት እይደለም ካሉ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይኸንን ባህላዊ ገጽታ እግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። የቅዱስ መስቀል ቅዱስ ምስል የሃይማኖት ምልክት ብቻ ሳይሆን የባህል ምልክትም ጭምር ነው፣ በአሁኑ ወቅት የባህል አምባ ገነናዊ እና ፈላጭ ቆራጭ፣ ማመን አለ ማመን ሁሉም ያው ነው፣ የሚለው የእሴቶች መኖር እና ያላቸው ቅደም ተከታላዊ ሂደት ብሎ የለም የሚለው የተዛማጅ ባህል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ደብዛዛ ማወቅ እንጂ ሙሉ እወቅት የለም፣ ሙሉ በሙሉ ለማወቅ አይቻልም የሚለው ባህል እና የስነ ዓለማዊነት ባህላዊ አምባ ገነን እየተስፋፋ ነው ያሉትን ሐሳብ በመጥቀስ፣ የተጠቀሰው የባህል ዓይነት፣ ሃይማኖት የግል ጉዳይ፣ ማኅበራዊ መግለጫ እንዳይኖረው የሚያስገድድ እና የቤተ ክርስትያን አንቀጸ ሃይማኖትን የሚጻረር መሆኑ አስረድተው፣ የሃይማኖት ነጻነት መከበር የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ ያስገድዳል፣ ስለዚህ የሃይማኖት መግለጫ የሚቃወም ሁሉም አምባ ገነናዊ አመለካከት ነው ብለዋል።

የሥነ መብት እና ግዴታ መምህር የሕግ ሊቅ እና የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሕግ አማካሪ ፕሮፈሶር ቨነራንዶ ማራኖ በበኩላቸውም በቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የስትራስበርግ ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ውሳኔ የቅዱስ መስቀል ቅዱስ ምስል በትምህር ቤቶች እንዳሰቀል በማለት የሰጠው ፍርድ፣ ማንም የጠበቀው አልነበረም ሆኖም ብዙ አገሮች ቤተ ክርስትያንም ሳይቀር ይህ የሃይማኖት መግለጫ ምልክቶች በይፋ መስቀል እና ሃይማኖትን መግለጥ ባህርያዊ መብት መሆኑ ዳግም ለመገንዘብ አነቃቅተዋል፣ በሌላው ረገድም የሃይማኖት ነጻነት ዳግም በሚገባ ተጢኖ እንዲከበር ለማድረግ የሚያነቃቃ ባህላዊ አመለካከት አስፈላጊ መሆኑ ይጠቁማል ብለዋል።

በዚህ በተካሄደው አውደ ጥናት የሮማ ከተማ ከንቲባ ጃኒ አለማኖ ንንግር ሲያሰሙ፣ ከሃይማኖት እና ከባህል ማምለትጥ ሳይሆን ማንነትህን ለማወቅ እና በህይወትህ ምን ለመሆን እንደምትሻ ለመለየት ከሃይማኖት እና ከባህል ጋር መነጻጸር ግድ ነው በማለት በትምህርት ቤቶች ቅዱስ ምስል ቅዱስ መስቀል እንዳይኖር የሚያዘው ውሳኔ የዓለማዊነት ባህል እና ርእዮት አምባገነናዊነትን ያንጸባርቃል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.