2010-06-23 16:35:57

ሮብዓዊ ትምህርተ ክርስቶስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እንደተለመደው ዛሬ ረፋድ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለምእመናን ሮብዓዊ አስተምህሮ ሰጥተዋል።

ቅድስነታቸው ባለፉት ሁለት ግዝያት የሰጡቱ ትምህርተ ክርስቶስ ቅዱስ ቶማስ ዘ አኲኖ ትኩረት የሰጠ መኖሩ አስታውሰው ዛሬ ሶስተኛውን ክፍል እንደሚያጠቃልሉ ጠቅሰው ፡ ከቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ ብዙ መማር እንችላለን ብለዋል።

ከኔ በፊት የነበሩ ነፍስሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ የቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ የሞተበት ሰባኛ ሚእተ ዓመት ምክንያት በማድረግ እኤአ በ1974 ፎሳኖቫ ላይ መምህር ቶማስ የትኛው ትምህርት ትሰጠናለህ ብለው ራሳቸው ይጠይቁ እና፡ ቅዱስ ቶማስ ዘ አኲኖ የተከላከለለት በሐቅ ላይ ያለውን የካቶሊክ ሃይምኖት እምነት ብለው መመለሳቸው አስታውሰዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ቅዱስ ቶማስ ዘአኪ1ኖን በመጥቀስ ሁላችን የቤተክርስትያን ታማኝ ልጆች ነን ያሉትን ዘክረዋል።

አያይዘው ቅዱስ ቶማስ ቅዱሳን መጻሕፍት እና የቤተክርስትያን አባቶች በተለይ የቅዱስ አጎስጢኖስ ትምህርት በጥልቅ በጥንቃቄ መፈተሹ ማጥናቱ መመርመሩ አስታውቀዋል።

ከዚያ ባሻገርም የጥንታውያን ፍላስፋዎች በተለይ የአርሲቶል የአስተሳሰብ ዘዴ በጥሞና በማጥናት የእምነት ሐቅነትን ለመቅረጽ መቻሉ አመልክተዋል።

ቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ ያድረገው ጥረት በጸሎት እና ከሰማይ በሚወርድ ብርሃን የተሸኘ መኖሩ አስገንዝበው ፡ ቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ የእግዚአብሔር ህልውና በተመለከተ ከሶስት የተለያዩ ዘዴዎች እንደሚነሳ ጠቅሰው፡ እግዚአብሔር ራሱ ህያው መሆኑ የሁሉም ነገራት የመጀመርያ እና መጨረሻ ስለሆነ ፍጥረታት ሁሉ የሱ ጥገኛ መሆናቸው ያስተምረናል ብለዋል።

እግዚአብሔር በማንኛውም ሕይወት ላት በምሕረቱ በክርስቶስ እና በሚስጢራት በኩል ህያው መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ ትምህርት ተንተርሰው አመልክተዋል።

የትምህርተ ክርስቶስ እና ቅዱስ መጽሐፍ ውነኛ ዓላማ እግዚአብሔርን ማስተዋወቅ እና ከሄሉ ኩሉ እግዝአብሔር በሁሉም ነገሮች በተለይ አእምሮ ባላቸው ፍጥረታት ሁሉ አልፋ እና ኦሜጋ የመጀመርያ እና የመጨረሻ መሆኑ ለማስገንዘብ መሆኑ ቅድስነታቸው የቅዱሱ ትምህርት ሰጥተው አስገንዝበዋል።

የቤተክርስትያን ሊቅ ቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ እንደምያስተምረን ክርስቶስ ለሰው ልጅ መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ፍጹም ሰው እና ፍጹም አምላክ በመሆን በመሀከላችን መገኘቱ የእግዚአብሔር ምስጢር መሆኑቅድስነታቸው በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምእመናን ገልጠዋል።

ሮብዓዊ አስተምህሮአቸው ሲጀምሩ ከቅዱስ ቶማስ ዘ አኲኖ ብዙ መሠረታዊ ዕውቀት ለመማር እንችላለን ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ቅዱሱ ዋቢ በማድረግ የሰው ልጅ በመንፈስ ቅዱስ ምህረት ተገፍቶ ግዝያዊ እና ዘለአለማዊ ደስታ ለማግኘት እግዚአብሔርን የማወቅ እና የመውደድ ዝንባሌ አለው ።

በማያያዝ ቅዱስ ቶማስ ዘአኲኖ ወደ እግዚአብሔር መድረስ የሚያስችለን መንገድ እና ሐቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ምስጢር ጠንቅቆ አጥንቶዋል ብለዋል ።

ሮብዓዊ ትምህርቱ እንደተጠናቀቀ ለምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.