2010-06-15 10:29:18

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የኤውሮጳ የእድገት ባንክ ምክር ቤት አባላት ተቀብለው አነጋገሩ ፡


የኤውሮጳ እደገት ባንክ ምክር ቤት ስብሰባ እዚህ ቫቲካን ውስጥ ዓመታዊ ስብሰባ እየካሄደ መሆኑ የሚታውቅ ሲሆን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የዚሁ ስብሰባ ተሳታፊዎች ተቀብለው ማነጋገራቸው ተመልክተዋል።

ቅድስነታቸው በዚሁ ግንኙነት ለምክር ቤቱ አባላት እንደገለጡላቸው፡ በዓለም ላይ የኤኮኒሚ ቀውስ በተደቀነበት ግዜ የቀውሱ ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘት የክርስትያን እሴቶች ምርኩስ በማድረግ መፍትሔ ማፈላለጉ እጅግ ጠቃሚነው ።

ኤውሮጳውያን የክርስትያን እሴቶችን ወደ ጐን መተው የለባቸውም ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ፡ የክርስትያን እሴቶች የኤኮኖሚ እና ማሕበራዊ መንቀሳቀሻ ሞቶር መሆናቸው ማስገንዘባቸው ግንኝነቱ የተከታተሉ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አስታውቀዋል።

ባለፈው መጨረሻ ሚእተ ዓመት ኤውሮጳ ውስጥ የተከሰቱ የፓሊቲካ መርሆዎች ኤውሮጳ በሁለት ሳንባዎች ለመተንፈስ መርዳታቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ላነጋገርዋቸው የኤውሮጳ የእድገት ባንክ ምክር ቤት አባላት ማመልከታቸው መገናኛ ብዙኀኑ ዘግበዋል።

በምዕራብ እና ምስራቅ ኤውሮጳ ሀገራት የኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ልውውጥ መደረጉ በማልከትም እውነታዊ ሰብአዊ እድገት ተድረገዋል ወይ በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መጠየቃቸው መገናኛ ብዙኀኑ አመልክተዋል።

የምስራቅ ኤውሮጳ ፈላጭ ቁራጭ የፓሊቲካ ርእዮተ ዓለም መወገድ ለኤኮኖምያዊ ጠቀሜታ ብቻ ነው ወይ በማለት እንደገና የጠየቁ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሰብአዊ ክብሮች የሚጠብቅ እድገት ለማግኘት ጭምር እንጂ በማለት መመለሳቸው ተያይዞ ተገልጠዋል።

የኤውሮጳ መንነት በጥንታዊ የክፍለ ዓለሚቱ መንፈስ መታነጻቸው መረሳት እንደማይገባ ቅድስነታቸው በማያያዝ መግለጣቸውም ተመልክተዋል።

ስለሆነም አሁን በአጠቃላይ ዓለማችን በተለይ ኤውሮጳ የገጠማትን የኤኮኖሚ ቀውስ በፋይናንሳዊ ዓይን ብቻ መታየት እንደሌለበት ጠቅሰው ካሪታስ ኢን ቨሪታተ ፍቅር በእውነት ላይ የተሰየመ ራሳቸው የጻፉትን ሐዋርያዊ መልእክት አስታውሰው የእግዚአብሔር ፍቅር ሐቀኛ ኤኮኖምያዊ እና ፖልቲኡካዊ ኀይል መሆኑ መዘነጋት እንደማይገባ መግለጣቸው ተገልጸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናንትና የኤውሮጳ እድገት ባንክ ምክር ቤት አባላት ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ እንዳመልከቱት ክሰው ፍጥረት የሚበልጥ ማንኛውም ነገር የለም እና የኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ይዘታዎች የሰው ልጅ እና ክብሩ ማእከል ያደረጉ መሆን ይጠበቅባቸዋል በማለት ለአባላቱ መግለጣቸው ግንኝነቱ የተከታተሉ መገናኛ ብዙኀኑ ገልጠዋል።

ቅድስነታቸው ንግግራቸው በማያያዝ ክርስትና የመንፈሳዊ እና ግብረ ገብነት ምንጭ እና የኤውሮጳ ህዝቦች ሀብት መሆኑ መግለጣቸው ተዘግበዋል።

እንደሚታቀው ቅድስት መንበር ከ1973 እኤአ የዚሁ የኤውሮጳ እድገት ባንክ ምክር ቤት አባል መሆንዋ የሚታወስ ነው ።

ይህ በዚህ እንዳለ የኤውሮጳ የእድገት ባንክ ምክር ቤት ስብሰባ ሲከፈት የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እዚያው ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፡

ቅድስት መንበር የኤውሮጳ አንድነት ደጋፊ መሆንዋ አመልክተው ሕብረቱ እውን እንዲሆን የሰሩ ቀደምት አባቶች ኤውሮጳ ክርስትያናዊ እሴቶችዋ የጠበቅች ትሆን ዘንድ ትሆን ከፍተኛ ጥረት ማካሄዳቸው ገልጸዋል።

በዓለማችን ላይ ሰላም መረጋጋት ትብብር እና እድገት እንዲደገንኝ ትኩረት በመስጠት የምትራመድ ኤውሮጳ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ድጋፍ እንደምታገኝ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ መግለጣቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.