2010-06-14 14:49:41

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ፣ የክህነት ዓመት


የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አሰዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ የክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ፣ የክህነት ዓመት ለእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ለመላው ህዝበ ክርስትያን RealAudioMP3 ዓቢይ ጸጋ መሆኑ ገልጠው፣ መላ ውሉደ ክህነት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥር በመመራት ያከበሩት ዓቢይ በዓል ነው ብለዋል።

የክህነት ዓመት መዝጊያ በዓል የእምነት የጥሪ በጸሎት የተከበረ በዓል መሆኑ ገልጠው፣ ክህነት ሙያ እንዳልሆነ ቅዱስ አባታችን በመደጋገም በተለይ ደግሞ በመዝጊያው ዕለት በማሳሰብ፣ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ ነው እንዳሉ አስታውሰዋል። እግዚአብሔር የእርሱን ቃል የሚናገሩ የእርሱን የማዳን እንቅድ የሚያበስሩ ሰዎችን ይመርጣል፣ ለእነርሱም ይህ ዓቢይ ኃላፊነት ያለብሳል፣ እነዚህ ካህናት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተቃጠሉ፣ የመንግሥቱ ቅናት ያላቸው መሆን እንደሚጠበቅባቸው ቅዱስ አባታችን በማሳሰብ፣ በራስ ኃይል ሳይሆን ኃይል በሚሰጠው በእግዚአብሔር ኃይል የሚቻል የሚኖር ሕይወት ነው። ስለዚህ ክህነት ጸጋ እንጂ የግል ብርታት ምርጫ አይደለም፣ ቤተ ክርስትያን አለ ክህነታዊ ጸጋ አትኖርም፣ ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔር የማሳውን ሠራተኞች ይልክ ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል፣ በክህነት ዓመት መዝጊያ መርሃ ግብር መሠረት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቅዱስ ቁርባን ፊት የተፈጸመው አስተንትኖ የሚቀጥል እንደሚሆንም በርእሰ አንቀጹ አረጋግጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.