2010-06-14 14:44:47

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. መልእክት ለ 32ኛ ከማቸራታ ሎሬቶ የሰላም የእግር ጕዞ


ሁሌ በየዓመት በኢጣሊያ ከከተማ ማቸራታ እስከ ሎሬቶ የሰላም የእግር ጉዞ እንደሚካሄድ የሚዘከር ሲሆን ትላትና 32ኛው የሰላም የእግር ጉዞ ምዕራፍ መከናወኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ ከማቸራታ የተነሳው በከተማይቱ ሊቀ ጳጳሳት RealAudioMP3 ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ጁሊዮዶሮ ተመርቶ ለተካሄደው 32ኛው የሰላም የእግር ጉዞ፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የፈረሙበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

የሰላም የእግር ጉዞ ብፁዕ ካርዲናል ካርሎ ካፋራ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ መጀመሩ ሲገለጥ፣ ከተለያዩ የኢጣሊያ ከተሞች የተወጣጡ ካህናት ምእመናን የተሳተፉበት የሰላም ጉዞ፣ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በጽሞና በጸሎት እና ባስተንትኖ የተመራ የሰላም የእግር ጉዞ ሎሬቶ በሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የሚጠናቀቅ መሆኑ አለ ምክንያት እንዳልሆነ ሲያብራሩ፣ የማርያም የእምነት አብነት ለማጉላት እና ለመከተል ታስቦ መሆኑ ገልጠው፣ ክርስትያኖች የማርኬ ተወላጅ የሆኑት የቤተ ክርስትያን ልጅ የአባ ማተዮ ሪቺ አብነት ጭምር እንዲከተሉ ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ የዘንድሮ የእግር ጉዞ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ግንቦት 29 ቀን 2010 ባበሩት ችቦ የተመራ እንደነበርም ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ የሰላም የእግር ጉዞ ችቦ በተለያዩ የኢጣሊያ ከተሞች ዑደት ሲያደርግ መቆየቱ እና ባለፈው ዓመት በርእደ መሬት አደጋ ለተጠቃው ሕዝብ መንፈሳዊ ድጋፍ ለመሰጠት በላኵይላ ከተማ በኵል የእግር የሰላም ጉዞ በመምራት ሎሬቶ መድረሱ ሲገለጥ፣ በሚቀጥለው ዓመት በማድሪድ ከነሓሴ 16 ቀን እስከ ነሓሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ሊካሄድ ተወስኖ ባለው ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን ዑደት እንደሚያደርግም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.