2010-06-14 14:48:07

ብፁዕ ካርዲናል ሂዩመስ፣ የክህነት ዓመት ሂደት


የካህናት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ሂዩመስ የውሉደ ክህነት ጠባቂ ቅዱስ ኩራቶ ዳርስ በሰማይ ቤት የተወለደበት 150ኛው ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ሰኔ 19 ቀን ተጀምሮ ባለፈው ዓርብ በቅዱስ ልበ እየሱስ ዓመታዊ በዓል የተፈጸመው የክህነት ዓመት አስመልክተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር RealAudioMP3 ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በቅድሚያ በመዝጊያው በዓል ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ከ 15 ሺሕ በላይ ካህናት መሳተፋቸው አስታውሰው፣ የሚያስደንቅ ሱታፌ መታየቱንም ገልጠው፣ የካህናቱ ተሳትፎ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር ብለዋል።

የክህነት ዓመት እንዲከበር ቅዱስ አባታችን ካወጁበት ዕለት ጀምሮ በሁሉም አገሮች በምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ መንፈሳዊ ባህላዊ መርሃ ግብሮች ተሸኝቶ ሲከበር መቆየቱ ገልጠው፣ በእውነት ሂደት አወንታዊ ነበር ብለዋል። ካህናት ማንም የማይፈጽመው ሚሥጢራትን የመሥራት ጸጋ የተሰጣቸው ናቸው። ስለዚህ ክህነታዊ ልብ ሊኖራቸው ያስፈልጋል፣ በክህነት ጥሪ እራስህን በቤተ ክርስትያን ከቤተ ክርስትያን ጋር ለእግዚአብሔር አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እነሆኝ ብለህ እግዚአብሔር ለሚሰጥህ መንጋ ማገልገል መሆኑ አብራርተው ይህ ደግሞ የካህን የደስታ ምክንያት ነው ብለዋል። ካህን ይላሉ ብፁዕነታቸው መንፈሳዊ ባህላዊ ጥበብ የተካነ፣ የሚኖረውን የሚሰብክ የተልእኮ ጥሪ፣ እርሱም ወንጌልን ለሁሉም ለማዳራስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላላወቅቱ እንዲያውቁት የሚለውን የቤተ ክርስያን ተልእኮ የሚኖር መሆን አለበት ብለዋል።

ሁሉም የቤተ ክርስትያን የአንድነት ምልክት ከሆኑት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ውህደት ባላቸው ብፁዓን ጳጳሳት ተመርተው በአንድነት፣ የካህን ክህነታዊ መለያው በጥንቃቄ የተስተነተነበት ዓመት እንደነበር ገልጠው፣ አስተንትኖው በክህነት ዓመት ተገባደደ ማለት ሳይሆን የሚቀጥል ነው። እግዚአብሔር ለክህነት ሕይወት የጠራቸው ወጣቶች አለ ምንም ፍራት ጥሪያቸውን የመከተል ብርታት ያገኙ ዘንድ የተጸለየበት ዓመት ነበር፣ ወጣቶች ለጋሾች ይሆኑ ዘንድ ስለ እነርሱ ዘወትር መጸለይ አለብን ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.