2010-06-12 09:15:20

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት መልእክት፣ የክህነት ዓመት


ምስጋና መለወጥ እና ጽናት በሚሉት ሶስት ቃላት የሚጠቃላለ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ውሳኔ መሠረት በይፋ በእነተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን መከበረ የጀመረው እና እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው የክህነት ዓመት ምክንያት ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ እና ስነ ቤተ ክርስትያናዊ መልእክት አዘል ለመላ RealAudioMP3 የኢጣልያ ካህናት ምልእክት ማስተላለፋቸው ተገልጠዋል።

የኢጣሊያ ብጹዓን ጳጳሳት፣ ካህናቶቻቸው አመስጋኞች እንዲሆኑ ዕለት በዕለት በመለወጥ ጎዳና የሚራመዱ እና በጥሪያቸው መኖር የበረቱ አገልጋዮች ሆነው ይኖሩ ዘንድ አደራ በማለት፣ የአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት ወንጀል መሠረት በመላ ካህናት ላይ የሚነዛው ጅምላዊ ክስ ና የሚሰጠው ፍርድ ተስፍ ሳያስቆርጣቸው ለደከሙት እንዲጸልዩ ብርታትን ከእግዚአብሔር እንዲያገኙ መለመን እንደሚጠበቅባቸው ብፁዓን ጳጳሳት በማሳሰብ፣ በዚህ አቢይ የክህነት ዓመት መዝጊያ በሚፈጸሙት የሊጡርጊያ ሥነ ሥርዓቶች አማካኝነት ውህደት እና መቀራረብ ይመሰከር ዘንድ አደራ ብለዋል።

በእናንተ ይላሉ ብፁዓን ጳጳሳት ለካህናቶቻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁነው ኩሩዎች ነን፣ ካሉ በኋላ ለመለወጥ እና ለንስሐ አደራ በማለት፣ በሐጢአት እና በሰብአዊ ኢፍጹምነት ምክንያት ተስፋ ሳይቆርጡ ዕለት በዕለት የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ፣ ቅዱሳን እንዲሁን ብለዋል። በመጨረሻም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እኔ ኑ፣ ከእኔ ጋር በመሆን፣ እኔን ተከተለኝ፣ የሚለው ክርስቶሳዊ ትእዛዝ ለሁሉም ነው። ቤተ ክርስትያን ለመንገዳችን ብርሃን ለጉዞችን መንገድ የሆነውን ወንጌል ለሁሉም ለማዳረስ ኃላፊነቱን እንዳለበሰቻቸውም አስታውሰው፣ በክህነት መኖር ቀላል ባይሆንም በእውነተኛ ሕይወት ከሚጠራው ጋር ከተኖረ ከእርሱ ጋር በእርሱ የማይቻል ምንም ነገር የለም፣ ቢወደቅም ተነስቶ ከእርሱ ጋር መራመድን እትዘንጉ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.