2010-06-11 13:35:01

ቱርክ፣ ቤተ ክርስትያን ብትሰቃይም ፈጽማ ተስፋ አትቆርጥም


እ.ኤ.አ. ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ.ም የቱርክ ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የአናቶሊያ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ፓዶቨሰ መገደላቸው የሚዘከር ሲሆን፣ የአቡነ ፓዶቨሰ መገደል በመጥቀስ በቱርክ ለጳጳሳዊ ልኡካን ማኅበር አስተዳዳሪ RealAudioMP3 የፍራንቸስካውያን ማኅበር አባል አባ ማራቲን ክመተክ፣ ቤተ ክርስትያንን በማሳደድ አባላቶችዋ ለሞት በመዳረግ ለስቃይ ማጋለጥ ይቻላል፣ ነገር ግን ቤተ ክርስትያን ተስፋ ማስቆረጥ የማይቻል ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ፓዶቨሰ በህዝብ የተወደዱ እና የሚደነቁ እንደነበሩም አባ ክመተክ አስታውሰው የሳቸው መገደል አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት የሁሉም ልብ በጥልቀት የነካ ሃዘን አስክትለዋል። የቱርክ ማኅበረ ክርስትያን በተደጋጋሚ በካህናት እና በቤተ ክርስትያን ላይ የሚደረሰው አደጋ እንዳስደነገጣቸውም በማብራራት፣ ክርስትያን ምእመናን በቱርክ መኖር ወይንም መሰደድ በሚለው ጥያቄ እንዲወጠር ማድረጉ ገልጠዋል።

ምንም’ኳ የቱርክ መራሄ መንግሥት ረሰፕ ታይፒ ኤድሮጋን የውሁዳን ሃይማኖት ምእመናን ሕይወት ጥበቃ በሚል እቅድ የአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች እነዚህ የክርትስያን እና የአይሁድ ውሁዳን ምእመን የሕይወት ዋሳትና እንዲረጋገጥ ውሳኔ ያስተላለፉ ቢሆንም፣ የውሁዳን ኃይማኖት ምእመናን ህልውና አሁንም ላደጋ የተጋለጠ መሆኑ የአባ ክመተክ ቃል የጠቀሰ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በቱርክ ብፁዕ አቡነ ፓዶቨሰ በተገደሉበት ኢስከንደሩም ከተማ የሚገኘው በአገሪቱ መንግሥት ውሳኔ መሠረት ሲኔማ ቤት እንዲሆን ተደርጎ የነበረው ጥናታዊው የቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስትያን ለአምልኮ እና ለመንፈሳዊ አገግልግሎት መከፈቱ ሲገለጥ፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በቱርክ የሚገኙት የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ልኡካን ያሳተፈ ለመክፈቸው ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የሶርያ ሥርዓት ለምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በአንጽዮካ ፓትሪያርክ ኢግናሰ ዩሲፍ ሶስተኛ ዩናን መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.