2010-06-11 13:33:12

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፣ እውነተኞች እና ነቢያት ካህናት


በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ካህናት ባሳዩት የታማኝነት ጉድለት አማካኝነት የቤተክርስትያን ታማኝነት ለአደጋ እንዳጋለጡ በመጥቀስ፣ ኅብረተሰባችን እውነተኞች እና የኅዳሴ ዓለም ነቢያት ካህናት እንደሚያስፈልገው ከትላንትና በስትያ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ የክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያት “የወቅቱ ካህናት” በሚል ርእስ ሥር አፍቅሮተ ዘቤት ማለትም ፎኮላሪኒ RealAudioMP3 በመባል የሚጠራው የካቶሊክ እንቅስቃሴ እና ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ተኃድሶ ማኅበር እንዲሁም ሌሎች የካቶሊክ ማኅበራት እና እንቅስቃሴዎች በጋራ አነሳሽነት በተዘጋጀው ጉባኤ የሥነ ጥበብ እና የምስክርነት መርሃ ግብር በተፈጸመበት ጉባኤ በመገኘት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ለተሳታፊዎች ያስተላለፉት መልእክት በማንበብ ንግግር ያሰሙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፉ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ገልጠዋል።

ተሳታፊያን ካህናት ከተለያዩ 70 አገሮች የተወጣጡ እንደነበሩም ለማወቅ ሲቻል፣ ጉባኤው የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ሁመስ በመሩት ጸሎተ ሠርክ መጠናቀቁ ተገልጠዋል።

በዚህ በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ በተካሄደው የስነ ጥበብ እና የምስክርነት መርሃ ግብር ከብራዚል የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ዋና ጸሓፊ አባ ማሪዮ ስፓኪ፣ ከሃንጋሪ አባ ኢምረ ኪስ፣ ከብሩንዲ አባ ፓስተሩርት ማኒራምቦና የሚገኙባቸው ብዙ ካህናት ምስክርነት መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ትላትና በኢጣልያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ 11 ሰዓት የክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያት በሮማ የሚገኘው ጳጳሳዊ የምሥራቅ አቢያተ ክርትያን ተቋም ያዘጋጀው፣ ከምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን ከመጡት ተሳታፍያን ካህናት በጋራ በመገናኘት ለካህናት ቅድስና ማእከል ያደረገ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተፈጽመዋል።

የጸሎት ሥነ ሥርዓት ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ የምሥራቅ አቢያተ ክርትያን መንበረ ጥበብ ተማሪ ካህናት ታጅበው የመሩት የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያን የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብጹዕ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ይህ የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንዳበቃም ሁሉም በአንድነት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለክህነት ዓመት መዝጊያ ምክንያት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተመራው የዋዜማ ጸሎት ሠርክ መሳተፋቸው መግለጫው አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.