2010-06-09 14:22:12

ጆርጂያ፣ የቄልቄዶን አበው አስተዋጽኦ


ክርስትያን ቄልቄዶን እና ካውካሶ በሚል ርእስ ሥር የተመራ በጆርጂያ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ያዘጋጀቸው በትቢሊስ በሚገኘ ኢሊያ የመንግሥት መንበረ ጠብብ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 2 ቀን እስከ ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ዓውደ ጥናት፣ ተማሪዎች የመንበረ ጥበቡ አስተማሪዎች ምሁራን አካላት እና ምእመናን መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ በተካሄደው ዓውደ ጥናት የመንበረ ጥበቡ አፈ ጉባኤ RealAudioMP3 ጂጂ ተቭሳድዘ፣ በጆርጂያ ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ጁዜፐ ፓሶቶ በጆርጂያ ለሉተራን ቤተ ክርስትያን ጳጳስ ሃንስ ዮዋኪም ኪደርለን በጆርጂያ ለባፕቲስት ቤተ ክርስትያን ጳጳስ ማልክሃዝ ሶንጉላሽቪል ንግግር ማሰማታቸው ሲገለጥ፣ ከኢጣሊያ ከፈረንሳይ ከሩሲያ ከኡክራይን ከግሪክ የመጡ ምሁራን የቄልቄዶን አበው ማለት ቅዱስ ጎርጎሪያስ ዘ ኒሳ ቅዱስ ባዚሊዮስ አብይ የመሳሰሉት የሚገኙባቸው ለክርስትናው ሕይወት ምንኛ አስፈላጊ መሆናቸው የሚያረጋገጥ አስተምህሮ ማቅረባቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ጉባኤው በዚህ ዓይይነት ዓውደ ጥናት የጆርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ እና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ተቋሞች እንዲሳተፉ ለማስተባበር ጥረት እንዲደረግ አደራ እንዳለም ሲገለጥ፣ ዓውደ ጥናቱ የ 13ኛው ክፍለ ዘመን ተብሎ የሚነገርለት በቫርዚያ አርመንን እና ቱርክን በሚያዋስነው ክልል የሚገኘው የቀልቄዶን አበው ገዳምን በመጎብኝተ መጠናቀቁ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.