2010-06-09 16:19:34

የዓመተ ክህነት መዝጊያ መሥዋዕተ ቅዳሴ፡


ባለፈው ዓመት 2009 እኤአ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ ያረፈበት አንድ መቶ ሐምሳኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሀገራት አቀፍ ዓመተ ካህን መሰየማቸው የሚታወስ ነው።

ይህ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የታወጀው ዓመተ ካህን ፊታችን ሰነ አስራ ሀንድ ቀን እንደሚጠቃለል የሚታወስ ሲሆን የዓመተ ካህን መዝግያ መሠረት በማድረግ ከዘጠና ሀንድ ሀገራት የተውጣጡ ከዘጠኝ ሺ በላይ ካህናት ሮም ውስጥ እንደሚገኙ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ፡ ነገ ሐሙስ የዓመተ ካህን መዝጊያ ዋዜማ ካህናቱ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ተገኝተው የምስጋና ጸሎት ያደርጋሉ ።

ከነገ ወድያ ዓርብ ዕለት በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሚመራ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ የዓመተ ካህኑ ፍጻሜ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደሚከናወን መግለጫው በተጨማሪ አመልከተዋል።

በቫቲካን የቤተ ክህነት ማኅበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንጻ ትናትና በቅዱስ ዮሐን ዘ ላተራን ካተድራል ተገኝተው እዚያው ለተሰበስቡት ካህናት እና ምእመናን እንደገለጡት ፡

በመጀመርያ ደረጃ መንፈስ ቅዱስ ባይኖር ኖሮ ቤተክርትስያን ሰብአዊ ማኅበር ባልሆነች ነበር ።

በዓመተ ክህን መዝጊያ ምክንያት እዚህ ሮም ውስጥ የሚሰበሰቡ ከዘጠን ሺ በላይ ካህናት ከቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሚያስተሳስራቸው መንፈሳዊ ውስጣዊ ስሜት የሚያሳድሱበት ኦኣላማቸው በትክክል ለመወጣት አስተንትኖ እና ንስሐ እና ጸሎት የሚያደርጉበት ግዜ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንጻ ገልጠዋል።

ካህናት በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣቸው ሐላፊነት ከካዱ በእግዚአብሔርንንና በሰዎች ማለት በምእመናን ክህደት ፈጸሙ ብለን ለመናገር እንችላለን ያሉት ብፅዕነታቸው መዓርገ ክህነት ሲቀበሉ የተሰጣቸውን መንፈሳዊ ስጦታ አበላሹ ማለት መሆኑ አመልክተዋል።

ሐዋርያዊ እረኛ ማለት ራሱ እና ምእመናንን ወደ ቅድስና የሚመራ ንጹህ መሆን እንደሚጠበቅበትም ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንጻ ገልጠዋል።

በሐዋርያዊ እረኛነት እንድንመራው ሐላፊነታችን አውቀን በስከነ መንፈሳዊ አስተሳሰብ ማኅበረ ሰቦችን ካልመራን በአንጻሩ ወደ ክፋት የሚመሩ ሌትኩን ይችላሉ ያሉት ሊቀ ጳጳስ ማውሮ ፒያቸንጻ ካህናት የመንፈሳውነት እና የንጽህና አርአያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው ይህ ለሁሉ የቤተ ክህነት የቤተክርስትያን አባላት የሚመለከት መሆኑም በተጨማሪ አመልክተዋል።

ትናትና በዚሁ በቅዱስ ዮሐንስ ዘ ላተራን ባሲሊካ እደሳ በመንፈስ ቅዱስ የተሰየመው ማኅበር አባላት ተገኝተው መኖራቸው የትመልከተ ሲሆን በቅድስት መንበር የሰላም እና ፍትሕ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በብፁዕ ካርዲናል ፒተር ታክሶን የተመራ መስዋዕተ ቅዳሴ ተከታትለዋል።

ዛሬ ከቀትር በኃላም ቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ጳውሎስ አዳራሽ ሾንስታት በተባለ እንቅስቃሴ ካህናት ዛሬ በተሰየመ ርእስ ዙርያ የንግግር እና የሐሳብ መለዋወጥ መድረኽ ተካሄደዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና በቫቲካን የቤተ ክህነት ማኅበር መሪ ብፁዕ ካርዲናል ክላውድዮ ሁመስ በዚሁ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.