2010-06-09 14:23:23

አልጀሪያ፣ ይፍዊ ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ


በአልጀሪያ በቁስጥንጥንያ እና በሂፖ ሰበካዎች፣ ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና የክህነት ዓመት በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት መካሄዱ በአልጀሪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዳብሊው ዳብሊው ዳብሊው ኤይ ኤስ ኤስ ነጥብ ዲዘድ በተሰየመው ድረ ገጽ RealAudioMP3 በኩል ካስተላለፈው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በአሁኑ ወቅት በአልጀሪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በተመለከተ የቁስጥንጥንያ እና ሂፖ ሰበካዎች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፓውል ዴስፋርገስ መግለጫ ሲሰጡ፣ ምንም’ኳ ብዙ እክሎች እያጋጠማት ቢሆንም፣ የክርስቶስ ተከታይ ከመሆን በሚገኘው ኃይል አማካኝነት ሁሉን በእምነት ለመወጣት እና ለመጋፈጥ በማሳሰብ፣ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገውን ግኑኝነት እንዲሁም በአልጀሪያ ከሚገኙት ከ 300 ሺሕ በላይ ለሚገመቱት የሕገ ወጥ ስደተኞች ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው አገልግሎት ካብራሩ በኋላ የአልጀሪያ ቤተ ክርስትያን የሰማዕት የደም ፍሬ መሆኗ በመጥቀስ፣ የአፍሪቃ ሁለተኛው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና በአልጀሪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሚል ርእሰ ጉዳይ ጭምር ሰፊ አስተምህሮ እና ጥናት መከናወኑ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.