2010-06-09 14:18:12

ብፁዕ አቡነ ኬብሬአው፣ ሃይቲ እንዳትረሳ


እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ጥር 12 ቀን ሃይቲ ያናወጠው ርእደ መሬት በሰው ሕይወት እልቂት እና የንብረት መውደም አደጋ ማስከተሉ የሚዘከር ሲሆን፣ ርእደ መሬት በተከሰተበት ወቅት የመገናኛ ብዙሃን ስለ ሃይቲ ጉዳይ እና የተፈጥሮ አደጋ ያስከተለው አደጋ ለዓለም በማሳቁ ረገድ አቢይ የተገባ አገልግሎት የሰጡ ቢሆንም ቅሉ፣ ነገር ግን ትኵስ ወሬ ማሳደድ መርህ በማድረግ የሚራወጡ RealAudioMP3 በመሆናቸው ምክንያት፣ የሚከተሉት የተሳሳተ መመሪያ በአሁኑ ወቅት የሃይቲ የድህረ ርእደ መሬት ተጨባጭ ሁኔታ ምን እንደሚመስል እና የተጎዳው ህዝብ ድጋፍ እያገኘ ነውን ዳግመ ግንባታው እንዴትስ እየተካሄደ ነው የሚለውጥ ጥያቄ መሠረት መግለጫ እና ዜና ከማቅረብ የተቆጠቡ ሆነዋል ያሉት በፓሪስ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ የሚገኙት የኬፕ ሃይቲየን ሊቀ ጳጳስ የሃይቲ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ልዊስ ኬብሬአው የአለም ሕዝብ ሃይቲን እንዳይረሳ አደራ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በተለያየው ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያ ችግር በተጠቃችው ሃይቲ የወረደው ርእደ መሬት ችግሩ እጅግ ተባብሶ ዛሬ የአገሪቱ ሕዝብ በከፋ ለዘርፈ ብዙ አደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ ከፈረንሳይ ብጹዕን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የፓሪስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንድረ ቪንግት ትሮይስ ጋር በመገናኘ ንግግር ያሰሙት ብጹዕ አቡነ ከብረአው መግለጫ እጅግ አሳሳቢ እና ልብን በሃዘን የሚነካ መሆኑ የፈረንሳ ብፁዓን ጳጳሳት ቃል አቀባይ ብፁዕ አቡነ ቤርናርድ ፖድቪን ማሳወቃቸው ሲር የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.