2010-06-09 14:15:14

ቆጵሮስ፣ የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. የማበረታቻ መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 4 ቀን እስከ ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. በቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ መንበረ ጴጥሮስ መምለሳቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው በቆጵሮስ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት፣ በቆጵሮስ የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ረዳት ኣባ ኡምበርቶ ባራቶ ከቫቲካን ረዲዮ RealAudioMP3 ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 4 ቁጥር 32 “አማኞች ሁሉ አንድ ልብ እና አንድ አሳብ ነበራቸው” የሚለውን ቃል መርህ በማድረግ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ አስታውሰው፣ ምንም’ኳ የሁለት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ቢሆንም፣ ባንድ በኵል ጊዜው አጭር እና የሮጠ ቢመስልም ሁሉም ቆም ብሎ የተሳተፈበት መርሃ ግብር በመሆኑ የቅዱስነታቸው በቆጵሮስ ቆይታ ጊዜው እንዲቆም ያደረገው ይመስል ነበር ብለዋል።

መልእክታቸው እና አስተምህሮአቸው፣ ሁሉም የሚረዳው ጥልቅ እና በቀጥታ የሚናገር በተለይ ደግሞ ስለ ማኅበራዊ ሕይወት ስለ ፖለቲካው ዓለም የቆጵሮስ የካቶሊክ ማኅበረ ክርስትያን በተመለከተ የሰጡት አስተምህሮ፣ ቅዱሳት ጳውሎስ እና ባርናባስ ለቆጵሮስ የሰጡት አስተምህሮ የሚያስታውስ እና ያንን የሐዋርያት መንፈስ የሚያንጸባርቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማለትም በቅዱሳት ሐዋርያት በተሰበከችው አገር የተካሄደ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነበር ብለዋል። በቆጵሮስ የሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖቶች ለውህደት በማቅናት እንዲቀራረቡ እና እንዲወያዩ ያነቃቃ በአገሪቱ በሚገኙት ስደተኞች የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስያን በክርስትያን ባህል በጸናችው ቆጵሮስ መኖር ጸጋ ነው ብለዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ የማኅበረ ክርስትያን ህላዌ እጅግ አስቸጋሪ ቢሆንም ቅሉ ቅዱስ አባታችን በዚያ ክልል የሚኖረው ማኅበረ ክርስትያን ተስፋ ሳይቆርጥ እንዲኖር በማሳሰብ የማኅበረ ክርስትያን በመካከለኛው ምሥራቅ ህላዌ ጥሪ መሆኑ ማስረዳታቸው አስታውሰው፣ በቅድስት መሬት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ስፍራ እና ንብረት አስተዳዳሪ ኣባ ፒዛባላ የቅዱስ አባታችን መልእክት መሠረት ክርስትያኖች ክልላቸውን ጥለው እንዳይሰደዱ በማድረጉ ረገድ አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጡ መሆናቸው ኣባ ባራቶ አስታውቀው፣ የቅዱስ አባታችን የቆጥሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ውይይት መቀራረብ ሰላም እርቅ የሚሉትን ወንገላውያን እሴቶች ያጎላ መሆኑም ገልጠው፣ ከእግዚአብሔር የተላከ ምልክት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.