2010-06-09 14:19:49

ሊቢያ፣ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ


የትሪፖሊ መንግሥት በአገሪቱ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት ቅርንጫፍ ተሚሰጠው እንዲቋረጥ ያስተላለፈው ውሳኔ የኢጣልያ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት እጅግ አሳሳቢ ነው በማለት አስተያየት ሰጥጥቶበታል። RealAudioMP3

ይህ በሊቢያ የሚገኘው የስደተኞች እና የተፈናቃዮች የበላይ ድረገት ቅርንጫ ጽ/ቤት በአገሪቱ የሚገኙት ስደተኞች በሚገኙባቸው በተለያዩ 16 መጠለያ ሰፈሮች የተለያዩ ሰብአዊ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያ ድጋፍ ከመስጠት ባሻጋር የስደተኞች እና ተፈናቃዮች መብት እና ፈቃድ እንዲከበር በማድረጉ ሂደት አቢይ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ የሚሰጠው አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረግ በሊቢያ ለሚገኙት ስደተኞች ለከፋ ችግር እንደሚያጋልጥ የኢጣሊያው የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ምክር ቤት ሲያብራራ፣ የኢጣልያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፍራንኮ ፍራቲኒ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና የተፈናቃዮች የበላይ ድርገት ቅርንጫፍ በሊቢያ ለስደተኞች የሚሰጠው አገልግሎት ዳግም እንዲጀመር የሊቢያው መንግሥት ይፈቅድ ዘንድ ጥሪ አቅረበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.