2010-06-07 14:22:59

የክህነት ዓመት


ወደ ፍጻሜው በመቃረብ ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት በሮማ በሚካሄደው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሚመሩት የመዝጊያ ቅዳሴ፣ ከሆንግ ኮንግ ከማካዎ እና ከታይዋይ የሚመጡ ካህናት እንደሚሳተፉ ለማወቅ RealAudioMP3 ሲቻል፣ እነዚህ በዚህ የክህነት ዓመት መዝጊያ ወክለው ከሶስቱ ሰበካ እዚህ ሮማ የሚመጡትን ካህናት ተጠሪ ኣባ ፒተር ልዌንግ፣ የካህናት ኅብረት የሚከበርበት በዓል መሆኑ ገልጠው፣ የውህደቱን መንፈስ እና የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ውህደት የሚመሰክር መሆኑም አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሆንግ ኮንግ ሰበካ ረዳት ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ቻንግ የተመሩ የሆንግ ኮንግ ካህናት በዚህ ወደ ፍጻሜው በመቃረብ ላይ ባለው የክህነት ዓመት ምክንያት በሮማ ቅዱሳት ሥፍራ መንፈሳዊ ጉብኝት ሲያካሂዱ መቆየታቸው ሲገለጥ፣ እነዚህ ካህናት ከትላትና በስትያ ወደ መጡበት መመለሳቸው እና ያካሄዱት መንፈሳዊ ጉብኝት እጅግ እንደማረካቸው አባ ፒተር ልዌንግ ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.