2010-06-07 14:19:33

ወንጌላዊ እሴቶች፣ ምሕረት እና እርቅ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቆጵሮስ ስለ አካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስደግፍ በቆጵሮስ የማሮኒታ ሥርዓት ለምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ሱየፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ በመጀመሪያ ደርጃ በአንዲት ሐዋርያዊት አገር የሚደረግ ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ጠቅሰው፣ በዚህች ቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ ባርናባስ ሐዋርያዊ አገልግሎት RealAudioMP3 የፈጸሙበት የትንሳኤ ብሥራት የተቀበለ የመጀመሪያ ማኅበረ ክርስትያን አገር በሆነችው ቆጵሮስ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የጳውሎስ አብነት የተከተለ ነው፣ ስለዚህ ቀደምት የክርትስያን ማኅበረሰብ አገር በክርስትናው እምነት ያለባቸውን ኃላፊነት የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።

በሌላው ረገድ ቅዱስ አባታችን በቆጵሮስ ከሚገኙት ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን ጋር በመገናኘት በተለይ ደግሞ በቆጵሮስ የብዙሃን ሃይማኖት ከሆነው ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት፣ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል የሚካሄደውን የጋራው ግኑኝነት ያነቃቃ መሆኑ በመጥቀስ፣ የተለያዩ የሊጥርጊያ ሥርዓት ከሚከተሉት የካቶሊክ ምእመናን እና ብፁዓን ጳጳሳት ውሉደ ክህነት፣ ወንጌል በማበሠሩ ዓላማ እና ከጴጥሮስ ተከታይ ጋር ያላቸው ትሥሥር እና ውህደት እንዲሁም በተአዝዞ አንድነታቸውን ከሚመሠክርቱ ጋር በመገናኘት የአቢያተ ክርስትያን ውህደት አብነት ናቸው። በዚህ አጋጣሚም ቅዱስ አባታችን ጥቅምት 2010 ዓ.ም. በቫቲካን ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በዚህ ክልል የሚገኙት የካቶሊክ ኣቢያተ ክርስትያን በጋራ ወንጌልን እና ውህደትን እንዲመሰክሩ መጠራታቸው የሚያረጋገጥ ነው እንዳሉም ብፁዕ አቡነ ሱየፍ በማብራራት፣ ስለዚህ የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እርቅን እና ምህረትን በጠቅላላ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚያንጸባርቅ ለክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምሥራቅ ጸጋ መሆኑ የመሰከረ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው ብለዋል።

በዚህ አንጻርም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ታሪካዊ እና ቆጵሮስ በክርስትናው እምነት ያለባት ኃላፊነት ያመለከተ፣ ምዕራብን እና ምሥራቅን የምታገናኝ አገር መሆኗ የገለጠ መሆኑ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን በይፋ ያቀረቡት የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሥራ መመሪያ ሰነድ ዘንድ ተመልክቶ እንደሚገኝም አስታውሰው የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.