2010-06-07 14:24:39

ናይጀሪያ፣ የሕጻናት እልቂት

 


ከባለፈው ጥር ወር ጀምሮ በናይጀሪያ ሰሜናዊ ምዕራብ በምትገኘው በዛምፋራ ክልል በሕገ ወጥ ተግባር ማእድን በማውጣት ሃብት ለሚያካብቱ ቡድኖጅ ተቀጥረው የሚሠሩ ላቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናት በጠቅላላ 335 ለሞት RealAudioMP3 አደጋ መጋለጣቸው የአቡጃን መንግሥት ይፋዊ መግለጫ አስታወቀ።

የአገሪቱ መንግሥት ይህ በሕገ ወጥ ተግባር ማእድን የሚወጣበት ክልል እንዲዘጋ ማድረጉ ባስራጨው መግለጫ በማሳወቅ፣ በተለያዩ በማእድን ሃብታም በሆኑት የአገሪቱ ክልሎች በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ረገጣ አሳሳቢ መሆኑ፣ የተለያዩ የሰብአዊ ማኅበራት የሚያቀርቡት ክስ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ሕጻናት በሕገ ወጥ ተግባር ለተለያዩ ክብር ሰራዥ አደጋ ማጋለጡ ይህ ደግሞ በአፍሪቃ በማእድን ሃብት በታደሉ አገሮች በተደጋጋሚ የሚታይ መሆኑም ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.