2010-06-07 14:22:10

ስለ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ግንዛቤ


እ.ኤ.አ. በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ ከሰኔ 10 እስከ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚላኖ ከተማ የአምብሮዚዮስ የጳውሎስ ስድስተኛ ማኅበር ያነቃቃው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ግንዛቤ በሚል ርእሰ ጉዳይ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ RealAudioMP3 በቤተ ክርስትያን እና በውሉደ ክህነት እንዲሁም በምእመናን ሕይወት ምንኛ ግንዛቤ እንደሚሰጠው፣ ምን ያክል ተግባራዊ እየሆነ ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ እና ሰፊ ማብራሪያ ብሎም አስተምህሮ የሚቀርብበት ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ የሚካሄደው ዓውደ ጥናት የቲዮሎጊያ ሊቅ በካናዳ ኩይበክ በሚገኘው ላቫል መንበረ ጥበብ መምህር ጊለስ ሩዛየር፣ ብፁዕ አቡነ ጁሊዮ ብራምቢላ እና ብፁዕ አቡነ አድሪያኖ ካፕሪዮሊ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በቤተ ክርስትያን ሕይወት በሚል ርእስ ሥር ያካሄዱት ሰፊ እና ጥልቅ ጥናት መሠረት ያደረገ ዓውደ ጥናት እንደሚሆን ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ ዓውደ ጥናት ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን ጋር ለሚደረገው የጋራ ውይይት መሠረት እንደሚሆንም ሲገለጥ፣ የታሪክ ሊቅ ፊሊፐ ሼናውክስ፣ የቲዮሎጊያ ሊቅ ሉካ ብረሳኖ እና የቲዮሎጊያ ሊቅ ፋውስቶ ኮሎምቦ ጭምር አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.