2010-06-04 14:50:24

የአቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት ጅማሬ 100ኛ ዓመት


በስኮትላንድ ርእሰ ከተማ ኤዲምቡርግ የዛሬ 100 ዓመት በፊት ዓለም አቀፍ ወንጌል ተልእኮ ጉባኤ መካሄዱ እና ይኽ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ለውህደት ያነቃቃው የጋራው ውይይት አንድ ብሎ ያስጀመረ ጉባኤ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ በጋራው ለአንድነት የሚደረገው ጥረት በጋራ ለማክበር የሁሉም አቢያተ ክርስያን መንፈሳውያን መሪዎች በአንድነት እያካሄዱት ያለው ጉባኤ እፊታችን እሁድ እንደሚጠናቀቅ ተገልጠዋል። RealAudioMP3

የጋራው ውይይት የተጀመረበት 100ኛው ዓመት ለማሰብ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ልኡካን አባል እና የውህደት ደጋፍያን ማእከል ምክትል ሊቀ መንበር ተረዛ ፍራንቸስካ ሮሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ በዚህ ዓመት በማክሄድ ላይ ያለው ጉባኤ እና የዛሬ 100 ዓመት በፊት የተካሄደው ጉባኤ፣ ወንጌል የማስፋፋት ተልእኮ እንዴት መከናወን እንዳለበት እና የእግዚአብሔር ቃል የማይሻር ቢሆንም፣ ከተጨባጩ ወቅታዊው ሁኔታ ጋር ማዛመድ አስፈላጊ እና ያለንበት ወቅታዊው ጊዜ በዚህ ቃል ሥር ማንበብ አንገብጋቢ መሆኑ ያመለክታሉ፣ ሁሉም አቢያተ ክርስትያን በአስፍሆተ ወንጌል የሚፈጽሙት ትብብር፣ ለውህደት የሚያደርጉት ጎዞ የሚያጎለብት ነው ብለዋል።

ይህ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት ዓለም ዓቀፋዊ ሂደት ያለው እየሆነ መምጣቱንም ገልጠው፣ አቢያተ ክርስትያን በሚገኙበት አገር ለውህደት ያቀና የጋራ ግኑኝነት የሚያከናውኑ ቢሆኑም፣ ይህ ቅዱስ ዓላማ ዓለም አቀፋዊ መሆን አለበት። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ያለው የጋራው ግኑኝነት ዓለም አቀፋዊነት የሚያንጸባርቅ መሆኑ አስረድተዋል።

የጋራው ውይይት ቲዮሎጊያዊ መሠረት ያለው በመሆኑም ለመጪው የውህደት ሂደት መልካም እይታ እያሰጠው መሆኑ ገልጠው፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ ነው ሥጦታዎች ግን ይለያያሉ፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ይኸንን ኃሳብ በመከተል ለውህደት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች። ወንጌል ለሁሉም እንዲዳረስ እና አብሳሪዎች የታመኑ ሆነው እንዲገኙ እና ሁሉም ወንጌልን ለመቀበል ይችል ዘንድ፣ ውህደት እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ይህ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.