2010-06-04 14:48:24

የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ውህደት


ቅዱስ አባታችን በቆጵሮስ የሚያካሂዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ዛሬ መጀመራቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው የአቢያተ ክርስትያናት ውህደት እንዲረጋገጥ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን መንፈሳውያን መሪዎች በጋራ በጂያ ኪሪኣኪ ክርይሶፖሊቲሳ ቤተ ክርስትያን በተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተገኝተው ለተጋባእያኑ በግሪክ ቋንቋ አንደኛይቱ የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ አንድ ቁጥር ሁለት RealAudioMP3 “እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስ በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ” የሚለውን በመጥቀስ፣ ጸጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ በማለት ሰላምታን አቅርበው፣ የእንኳንድ አህና መጡ መልእክት ላቀረቡላቸው ለኢዩስጢንያ እና ለመላ የቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክሪስቶስቶሞስ ዳግማዊን እና እንዲሁም የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ውህደት እንዲረጋገጥ የጸሎቱን ሥነ ሥርዓት ያስተናገዱት ለቅዱስ አባታችን የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ላሰሙት፣ ለፓፎስ ሜጥሮፖሊታ ብፁዕ አቡነ ጊዮርግ፣ በከፍተኛ ወንድማዊ ስሜት ምስጋናን በማቅረብ፣ ሁላችን በወርቅ የተሸፈነቸው የቅስት እምቤት ቤተ ክርስትያን ውስጥ ለዚህ ቅዱስ ዓላማ ለጸሎት መሰብሰባችን አቢይ ጸጋ ነው። በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 13 ከቁጥር ከ1 እስከ 4 ያለውን ቅዱስ ቃል በመጥቀስ፣ ቆጵሮስ ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያ ሓዋርያዊ ተልእኮ የፈጸመባት አገር መሆንዋ በማስታወስ፣ በቁጥር ሶስት “በርናባስ እና ሳውል በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቂያ ሄዱ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ዘለቁ” የሚለውን ቃል በማበከር ጠቅሰው፣ በቆጵሮስ የአስፍሆተ ወንጌል ጅማሬው እና ሂደቱ ምን እንደሚመስል በመተንተን፣ በዚህ ሐዋርያዊ እምነት ሥር መሠረት የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ውህደት ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ መገንዘቡ እንደማያዳግት ነው ብለው፣ የአቢያተ ክርስትያን ልዩነት ተወግዶ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤት ክርስትያን የነበራትን ውህደት ዳግም ማረጋገጥ የሁላችን ኃላፊነት ነው ብለዋል።

ሐዋርያዊ እምነት የሁሉም አቢያተ ክርስትያን የውህደት መሠረት ጸጋ እና ለተልእኮም ጭምር ጥሪ ነው። እንደ ጳውሎስ እና ባርናባስ እያንዳንዱ ክርስትያን በተቀበለው የጥምቀት ምሥጢር አማካኝነት በውስጡ በሚቀለበው የነቢይነት ጸጋ መሠረት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን እና የእርቅ የምህረት እና የሰላም የሆነው ወንጌሉን እንዲመሰክር መጠራቱን በመተንተን፣ በዚህ አጋጣሚ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2010 ዓ.ም. በቫቲካን የሚካሄደው የመካከለኛው ምስራቅ ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ሓዋርያዊው እምነት የሚያነቃቃ፣ በሁሉም አቢያተ ክርስትያን መካከል የጠበቀ ውይይት እና ግኑኝነት እንዲኖር፣ በዚህ ክልል አስፍሆተ ወንጌልን የሚያነቃቃ እና የሌሎች አቢያተ ክርስትያን እና ማኅበረ ክርስትያን ተጠሪዎች በማሳተፍ ጸጋ የታደለ ጉባኤ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።

በመቀጠልም በአቢያተ ክርስትያን የዛሬ 100 ዓመት በፊት ስኮትላንድ ርእሰ ከተማ ኤዲምበርግ የተጀመረው የጋራው ውይይት በማስታወስ፣ የአቢያተ ክርስትያን አንድነት እንዲረጋገጥ ያነቃቃው መሠረታዊው ምክንያት፣ ልዩነቱ ለአስፍሆተ ወንጌል አቢይ እንቅፋት መሆኑ አቢያተ ክርስያን ካሳደሩት ጥልቅ ግንዛቤ መሆኑ በመጥቀስ፣ ቅንነት እና ትእግሥት በተካነው መንፈስ የተለያዩት አቢያተ ክርስትያን ያለፈው ያከራከራቸው እና እንዲለያዩ ያደረጋቸው ታሪክ ወደ ጎን በማድረግ፣ ለመቀራረብ የሚመራቸውን መንገድ በጋራ ይለዩ ዘንድ አደራ በማለት፣ የቆጵሮስ ቤተ ክርስትያን የምሥራቁን እና የምዕራቡን ዓለም የምታገናኝ ድልድይ ነች። ለአንድነት እና ለውህደት የሚደረገው ጉዞ አስቸጋሪ ቢሆም ቅሉ፣ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ርክስትያን እና የቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የጋራው ውይይት እንዲገሠግስ በማድረጉ ኃላፊነት አቢያ ሚና እየተጫወቱ ናቸው ብለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን የቆጵሮስ ቅዱሳት በተለይ ደግሞ የሴሌውቅያ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ቅዱስ ኤጲፋኒዮ እና እንዲሁን ቅዱስ ባርናባስ ቅዱሳት ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ሁሉም የእግዚአብሔር ቅዱሳት መላ ማኅበረ ክርስትያንን እንዲባርኩ እና የሓዋርያት እምነት ለማቀብ እና ለመኖር እንዲረዱ እና ሁሉም አቢያተ ክርስትያን በውህደት በፍቅር እና በሰላም መንገድ እንዲመሩ ጸልየው ያሰሙትን ንግግር ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.