2010-06-04 14:51:29

የመልካም እረኛ ምሳሌ


እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የክህነት ዓመት ተብሎ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን እንዲከበር ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በመካሄድ ላይ ያለ ወደ ፍጻሜውም በመቃረብ ላይ መሆኑም RealAudioMP3 ሲታወቅ፣ የክህነት ዓመት ምክንያት፣ ሮማ በሚገኘው በረጂና አፖስቶሎሩም ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ በሚገኘው በር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የጉባኤ አዳራሽ በመልካም እረኛ ምሳሌ በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ሰነ 8 ቀን 2010 እንደሚካሄድ ተገልጠዋል።

ይህ ጳጳሳዊ ረጂና አፖስቶሎሩም እና የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር በጋራ ያዘጋጁት ዓውደ ጥናት፣ በዚህ በያዝነው ዘመን የካህናት ማንነት በጥልቀት የሚስተነትን አስተምህሮ እንደሚቀርብ ለማወቅ ሲቻል፣ አስተምህሮ ከሚያቀርቡት ውስጥ የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲላን ክላውዲዮ ሂዩመስ፣ የዚህ ቅዱስ ማኅበር ኅየነተ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ዳሪዮ ካስትሪዮን ሆያስ፣ የሥርዓተ አምልኮና የቅዱሳት ምሥጢራ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ካኚዛረስ፣ ጳጳሳዊ የሕይወት ተቋም ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ፣ የሕይወት እና ስነ ምርምር ተቋም ተባባሪ ሊቀ መንበር ሉቾ ሮማኖ እንደሚገኙባቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በዚህ ሊካሄድ ተወስኖ ባለው ዓውደ ጥናት ለዘመናችን ካህናት ፍጹም አብነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ እና እርሱን በመከተል የአብነት ሱታፌ ጸጋን የታደሉት የአንዳንድ ካህናት የሕይወት ታሪክ እና መሥዋዕት እንዲሁም በአስፍሆተ ወንጌል የሰጡት አብነት፣ ከእነርሱም ውስጥ እ.ኤ.አ. በ1980 ዓመታት የካህናት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ የነበሩት የብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ኢኖቸንቲ፣ ቅዱስ ራፋኤል ጉይዛር እና ኣባ ብፁዕ ካሮሎ ኞኪ ጉዳይ በሚመለከት አስተምህሮ እንደሚሰጥ ሲገለጥ፣ ዓውደ ጥናቱ ብፁዕ ካርዲናል ሂዩመስ በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚጠናቀቅ ሲር የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.