2010-06-02 14:50:04

የኢጣሊያ የትብብር እና የድጋፍ ማእከል


ቸይስ በመባል የሚጠራው የኢጣሊያ የትብብር እና የድጋፍ ማእከል መሥራች ኣባ ማሪዮ ፒኪ በ 80 ዓመት እድሜአቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ሲገለጥ፣ ትላትና ጧት በብዙ ሺ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በቅዱስ RealAudioMP3 ዮሓንስ ዘ ላተራኖ ባዚሊካ የቀብራችው ሥነ ሥርዓት የርማ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ በመሩት የፍትሃት ቅዳሴ ተፈጽመዋል።

የወጣቶች ስቃይ በተለያዩ ሰብአዊ ማኅብራዊ ችግር የተጠቁት የወጣቶች ሸክም የራሳችው በማድረግ ለወጣቱ የተሟላ ሕንጸት፣ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ የክህነት ጥሪያቸውን በዚህ የአገልግሎት መንፈስ የኖሩት አባ ማሪዮ ፒኪ በማስታወስ ማኅበራዊ ፍትሕ እንዲረጋገጥ ልክ እንደ አባ ማሪዮ ሚኪ አቢይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት አባ ልዊጂ ቾቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን በሚደረገው ጉዞ በተለያዩ ችግር መራመድ አቅቶአቸው ሕይወት እስከ መጥላት የሚደርሱትን በመደገፍ እና በማጽናናት መጀመሪያ እግዚአብሔርን ቀጥሎም የእርሱ ፍትሕ መፈለግ ተቀዳሚ ጥሪአችን መሆኑ በማስታወስ፣ ስለዚህ ወሳኙ እግዚአብሔር የት እንደምንፈልገው ነው። አባ ፒኪ በስቃይ ላይ በሚገኙት ወጣቶች ዘንድ በመፈለግ ነበር ያገኙትም፣ በሕመም ላይ እያሉም እግዚአብሔርን እግኝቶ በቃኝ ማለት እንደማይቻል እና ዕለት ዕእለት እርሱን አግኝቶ መኖር እርሱን በማግኘት ማደግን የመሰከሩ፣ በኅብረተሰብ ዘንድ ኢፍትሃዊነት ሕገ ወጥነት የሞት ባህል የሚያስፋፉትን አካላት የወንጀል ቡድኖችን በመቃወም ኅብረተሰብን በማነጽ በሚደረገው ፍትህ የማንገሥ ተልእኮ በጸሎት እና በቅዱስ ቁርባን በመኖር ፍቅር በማስተጋባት የሁሉም ኅሊና በማነቃቃት የኖሩት ናቸው በማለት ገልጠዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.