2010-06-02 14:52:15

የተፈጥሮ ሃብት በትክክል መጠቀም


ሃምሳኛው የኮንጎ የነጻነት ዓመት በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር ባለፈው ቅዳሜ የአገሪቱ ተራ ዜጎች ያነቃቁት ስብሰባ መካሄዱ ሲገለጥ በዚህ በኪኒሻሳ የአገሪቱ ነጻነት እና የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ እና ድኽነት በሚል ርእስ ሥር ሰፊ ውይይት እና አስተምህሮ RealAudioMP3 መቅረቡ ለማወቅ ሲቻል፣ የኮንጎ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ግልጽ እና ለእገር እና ለዜጎች ጥቅም ያቀና መሆን እንዳለበት ያሳሰበው የኪኒሻሳው ጉባኤ፣ የኮንጎ የማዕድን አውጭ ኢንዳስትሪዎች እና መንግሥት የማዕድን ልማት ውጤት እና ገቢ በተመለከተ የሚያቀርቡት የዝርዝር መግለጫ የሚጋጭ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ቅሌት ሙስና የመሳሰሉት አገሪቱ ወደ ኋላ እያስቀራት ያለው ወንጀል እንዲወገድ ዘመቻ የሚያካሂደው ማኅበር የአገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት አለ ሕግ በግል እና በቡድን በመደራጀት ድርጅቶች አማካኝነት የሚደረገው የማዕድን ሃብት ብዝበዛ ለምን እንዳልተገታ፣ እነዚህ የወንጀል ቡድኖች ተከታትሎ ለሕግ ለማቅረብ እና በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር ያካበቱት ሃብት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለምን እንዳልገባ ጥያቄ በማቅረብ፣ አገሪቱ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ሆና እያለች በተለያዩ በተዋቀረ እና በተደራጀ የሕገ ወጥ ተግባር ምክንያት በድኽነት ጫንቃ ሥር እንደምትገኝ ስብሰባው በማብራራት፣ የአገር ሃብት ለማህበራዊ ልማት እና እድገት መዋል እንዳለበት ጉባኤ በኃይለ ቃል ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ብፁዓን ጳጳሳታ ምክር ቤት፣ ይህች በተፈጥሮ ሃብት የታደለቸው አገራቸው ያላት የተፈጥሮ ሃብት የመጠቀሙ ሂደት በሥነ ምግባር የተካነ ይሆን ዘንድ ማሳሰባቸው የሚዘከር ነው። ብፁዓን ጳጳሳት የተፈጥሮ ሃብት ጸጋ መሆኑም በማብራራት፣ ለአገር እና ለህዝብ ጥቅም መዋል አለበት እንጂ ለጥቂቱ ሃብት ማደለቢያ መሆን እንደሌለበት እና የተፈጥሮ ሃብት ለግጭት ለውጥረት ብሎም ለተገዥነት እና ለአዲሱ የቅኝ ግዛት ሥርዓት አደጋ እያጋለጠ መሆኑ እግምት ውስጥ በማስገባት የኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. የተፈጥሮ ሃብት ጉዳይ የሚከታተል ጳጳሳዊ ድርገት በማቋቋሙ ጉዳዩ ቀርቦ መከታተል እንደጀመረ ሚስና የዜና አገግሎት በማስታወስ፣ የተፈጥሮ ሃብት የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት ለጥቅም እንዲውል በማጣራት ለምርት የሚያቀርቡት ኅብረ ኢንዳስትሪዎች የግል ሃብት ከማካበት ፈተና ተላቀው የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ልማት ማነቃቃት እና ለአገሪቱ እድገት ደጋፍያን መሆን እንደሚጠበቅባቸው በማሳሰብ ይህ ደግሞ ኃላፊነትም ጭምር ነው ብለው እንደነበር የዜና አገልግሎቱ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.