2010-06-02 14:50:58

እምነት እና ምርምር


ከተለያዩ 24 አገሮች የተወጣቱ 27 ተማሪዎች የሚሳተፉበት በካስተል ጋንደልፎ የቅድስት መንበር የሥነ ከዋክብት የምርምር ማእከል ያዘጋጀው የዚህ ማእከል ተማሪዎች የነበሩት የስነ ከዋክብት ሊቃውንት እና አንዳንድ በተለያዩ RealAudioMP3 መናብርተ ጥበብ የዚህ የጥናት ዘርፍ አስተማሪዎች ያሳተፈ 12ኛው የከዋክበት ዘገምታዊው ለውጥ የሚያስተዳድረው የተፈጥሮ ንጥረ ነገር ሂደት በጥልቀት ለመረዳት በተሰኘው እቅድ የተመራ እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 27 ቀን 2010 የሚዘልቀው አውደ ጥናት ባለፈው ቅዳሜ መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ስለዚህ በዚህ የበጋ የእረፍት ወቅት የሚካሄደው አውደ ጥናት በማስመልከት የቫቲካን የሥነ ከዋክብት የምርምር ማእከል አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ኾሴ ፉነስ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዚህ ዓውደ ጥናት ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከታላቅዋ ብሪጣኒያ ከአርጀንቲና የመጡ የዚህ ማአክል ተማሪዎች የነበሩት ጭምር የሚሳተፉበት መሆኑ በማስታወስ፣ ይህ የቫቲካን የምርምር ማእከል የስነ እውቀት ማእከል ቤተ ክርስትያን የሥነ ምርምር ሂደት እና የስነ እወቅት ዘርፍ ምንኛ እንደምትደግፍ የሚመሰክር ነው፣ ቤተ ክርስትያን የሥነ ምርምር ሂደት በማነቃቃት ረገድ የሰው ልጅ እግዚአብሔር የሰጠው እእምሮ በትክክል እንዲጠቀምበት በማስገንዘብ ጥልቅ ትምህት የምትሰጥበት ማእከል ነው ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን በዚህ የላቀው የትምህርት ዘርፍ የመሰልጠን ዕድል ለሌላቸው ለድኾች አገሮች ተማሪዎች የትምህርት እድል በመስጠት በዚህ የትምህርት ዘርፍ እንዲሰለጥኑ በማድረጉ ረገድ አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት ላይ እንደምትገኘ አስታውሰው፣ በድኾች አገሮች የሚገኙት የሥነ ከዋክበት ሊቃውንት የሚያካሂዱት የሥነ እወቅት ምርምር የሚኖርበት አገር ካለበት ድኽነት አንጻር ግቡን ሳይመታ እንዳይቀር በዚህ የቫቲካን የሥነ ከዋክብት የምርምር ማእከል እንደሚደገፉም በዚህ አጋጣሚ አስታውቀው፣ እምነት እና ምርምር የሚደጋገፉ እንጂ የሚጻረሩ እንዳልሆኑ የሚመሰክር ውደ ጥናት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.