2010-06-02 14:49:07

ቅዱስ አባታችን፣ ቅድስት ማርያም ለንጹሕ ቤተ ክርስትያናዊ ጉዞ አብነት


ግንቦት የማርያም ወር ተብሎ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን በየዓመቱ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን የማርያም እምነት በማስተንተን የእርሷን አብነት ለመከተል ማርያማዊ ጸሎት በጥልቀት የሚፈጸምበት ወር ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. RealAudioMP3 እንደሚያስታውሱንም እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ከማርያም ጋር የምንኖርበት ወር ነው። ይህ የማርያም ወር እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ቫቲካን በሚገኘው አጸድ ተገኝተው የመዝጊያ አስተምህሮ እና ቡራኬ ማቅረባቸው የቅድስቲ መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስነታቸው የማርያም ወር መዝጊያ በቀረበው የዋዜማ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተገኝተው ማርያም ለንጹሕ የቤተ ክርስትያን ጎዞ አብነት እና እውነተኛው የቤተክርስትያን ጉዞ ትርጉም መህኗ ሲያስተምሩ፣ በዚህ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ማርያም ኤልሳቤጥን የጎበኘችበት በዓል በሚዘከርበት ዕለት የሚጠናቀቀው የማርያም ወር፣ ዓለም የኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ ናፍቆት እንዳለው በማብራራትም ቅን እና ነጻነት የተረጋገጠበት ሥልጣኔ እውን ይሆን ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

የግል እና እንደ ቤተ ክርስትያንም ያለን ኅልውና ከእኛ ባሻገር ወደ ውጭ ያተኮረ፣ እርሱም ከእኔነት እና ከተጋነነው የራስ መተማመን እና ርእሰ ማእከልነት ተላቆ ወደ ሌሎች የምንራመድበት ከተለያየ አካባቢ እና ማኅበረሰብ ጋር የምንገናኝበት ኅልውና መሆኑ በማስረዳት፣ ይኽ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚጠይቀን መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ ጉዞ እርሱ፣ ማርያም አብራን ከእኛ ጋር ትጓዝ ዘንድ ይመክረናል፣ ይህ ደግሞ በጉዞአችን ማርያም ረዳታችን በመሆኑ ልጅዋ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኛ ጋር መሆኑ ታረጋገጥልናለች።

ቅድስት ኤልሳቤጥ፣ የኅሙማን የአዛውንት የደከሙት ባጠቃላይ ፍቅርን እና እረዳታን ለሚሹት የሁሉም የሰው ዘር ምልክት ነች፣ በመካከላችን ፍቅር እና እርዳታን የሚጠቁ እርዱኝ የሚሉ ሊደረሱ የሚገባቸው ብዙ ናቸው፣ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁጥር 38 ማርያም “እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አግልጋይ ነኝ” በማለት የሁሉም አግልጋይ መሆንዋ የገለጸችበት ቃል እና ተግባር የእያንዳንዳችን ኅልውና ትርጉም ያበሥራል ብለዋል።

እኛ ለሌሎች ልናቀርበው የሚገባን ሃብታችን ኢየሱስ ነው፣ የሰው ልጅ እርሱን በመናፈቅ ላይ ነው፣ የእርሱን ተጠምተዋል፣ ምንም’ኳ ችላ ቢሉትም እንደማያስቸልጋቸው ቢያስመስሉም የእርሱ ናፍቆት አለባቸው። የምንኖርበት ኅብረተሰብ ኤውሮጳ በጠቅላላ አለማችን ኢየሱስ ያስፈልገዋል ካሉ በኃላ ባህላዊው ሥልጣኔአችን ለተረጋጋ እና ሰላም ለተካነው ለማኅበራዊ ሕይወት መተኪያ የሌላቸው ምሰሶ የሆኑት እውነት እና ፍትሕ ነጻነት እና ፍቅር በእውነት የነገሠበት በደስታ እና በኃላፊነት የምንኖርበት ይሁን ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን አስተምህሮ ከመስጠታቸው በፊት የዚህ የማርያም ወር ጸሎት መዝጊያ የመሩት የቫቲካን ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ፣ ባሰሙት ስብከት፣ እለቱ የሕይወት በዓል እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ወደኛ የወረደበት በመካከላችን የተገኘበት እለት የሚከበርበት ሕይወት የሚስተነተንበት የሕይወት ቀን ነው በማለት በአሁኑ ወቅት ደንዳናው የሄሮድስ ልብ የሚኖሩ ለሕይወት እምቢ የሚሉ እንዳሉ መግለጣቸው የቅድስት መንበር መገልጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.