2010-06-01 10:01:30

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መልአከ እግዚአብሄር ጸሎት ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር አብረው መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።

ቅድስነታቸው መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙት ግዜ ፡ የቅድስት ሥላሴ ምስጢር እና ፊታችን ዓርብ ቆጵሮስ ላይ ስለሚያካሄዱት የሶስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት የተናገሩ ሲሆን ፡ ክርስትያኖች የትእምርተ መስቅል ምልክት የሆነውን በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በማለት በሚጸልዩበት ግዜ የእግዚአብሔር ስም ያስታውሳሉ ሲሉ ገልጠዋል።

በፍጥነት የሚደረገው ትእምርተ መስቀል መለኮታዊ ቅድስት ሥላሴ እና ክርስትያን ከጠመቀ በኃላ በሱላ የሰረጸ ትእምርተ ክርስትያን መሆኑ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ማመልከታቸው ተመልክተዋል።

ጸሎት ስንጀምር የምናደርገው ትእምርተ መስቀል መንፈስ ቅዱስ በኛ ላይ እንዲወርድ ከጸሎት በኃላ በእግዚአብሔር የተሰጠንን አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በኛ ላይ እንዲኖር መሆኑ ቅድስነታቸው በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ በአስር ሺዎች ለሚገመቱ

ምእመናን ገልጠዋል።

የቅድስት ሥላሴ ምስጢር ማለት የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ትንሳኤ እና ዕርገት የእግዚአብሔር ስራ የሚያስታውስ መሆኑ ቅድስነቶም መግለጣቸው ተመልክተዋል።

በአብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ያለውን ግንኙነት ለመረዳት ከሰው እውቀት በላይ መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስረድተዋል።

ምስጢረ ጥምቀት እስከ ሕልፈት ድረስ ከክርስትያኖች እንደማይለይም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ ገልጠዋል።

ቅድስነታቸው ፊታችን ዓርብ ቆጵሮስ ላይ ለሶስት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ እና ከየመካከለኛው ምስራቅ ካቶሊካውያን አባየተ ክርስትናት ወኪሎች ጋርም እንደሚገናኙ ጠቅሰው ፊታችን ጥቅምት ወር የመከከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት ሲኖዶስ ቫቲካን ውስጥ እንደሚካሄድም አስታውሰዋል።

በመጨረሻም በስድስት የተለያዩ ቋንቋዎችም ለምእመናን ሰላምታ ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ተሰናብተዋቸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ክአንድ ዓመት በፊት መካከለኛው ምስራቅ ዮርዳኖስ እና ቅድስት ሀገር መጐብኘታቸው አስታውሰው አሁን ደሴት ቆጵሮስን ለመገብኘት መዘጋጀታቸው አመልክተው ጥንት የክርስቶስ ሐዋርያት በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ደሴቲቱን መጐብኘቱ ገልጠዋል።

ደሴት ቆጵሮስ የክርስትያን አንድነት ውይይት ማኸል መሆንዋ ቃል አቀባዩ አመልክተው ቅድስነታቸው ቆጵሮስ ላይ በሚያደርጉት ቆይታ Instrumenetum laboris የምግባረ ስራ ሰነድ ለመካከለኛው ምስራቅ ጳጳሳት እንደሚያስረክቡ ገልጠዋል።

ቆጵሮስ ክርስትያናዊ እሴቶች አዘል መሆንዋ የገለጹት የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ የቫቲካን ተለቪስዮን ማእከል እና ራድዮ ቫቲካን ዳይረክተር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ

ቅዱስ ባርናባስ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከሐዋርያት ጋር የተደባለቀ ሐዋርያ ቆጵሮሳዊ መሆኑ አስገንዝበዋል።

ቅዱሳን ጳውሎስ እና ዮሐንስ መጥምቅም በዚች ደስሴት እና አከባቢ ቅዱስ ወንጌል መስበካቸው ቃል አቀብዩ በማያያዝ አመልክተዋል።

በተለይ ቅዱስ ጰጥሮስ ሐዋርያ ከቆጵሮስ ተነስቶ በሞልታ በኩል ሮም መግባቱ ቅዱሳን መጻሕፍት በመጥቀስ አስረድተዋል።

ቆጵሮስ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የተያያዘች መንፈሳዊ እና ባህላዊ የክርስትና ማእከል መሆንዋ እና የመከከለኛው ምስራቅ እና ምዕራቡ ዓለም የኤስያ ክፍለ ዓለም እና ኤውሮጳ መስመር መሆንዋም የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስረድተዋል።

ይሁን እና አንድ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቆጵሮስ ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስድተኛ የመጀመርያ መሆናቸው ነው ።








All the contents on this site are copyrighted ©.