2010-05-29 18:16:32

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለጣልያን ጳጳሳት ንግግር አደረጉ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጣልያን ጳጳሳት ብፁዓን ጳጳሳት ተቀበለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመልክተዋል።

የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት አጠቃላይ ስብሰባ ቫቲካን ውስጥ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ቅድስነታቸው በዚሁ አጠቃላይ ስብሰባ ተስታፊ የሆኑ ጳጳሳት ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ እንዳመለከቱት ፡ የጣልያን ቤተክርስትያን ለሀገሪቱ ማኅበራዊ እና ግብረ ገባዊ እድገት አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባታል።

አሁን ባለንበት ግዜ የጣልያን ቤተክርስትያን በድጋሜ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል ማካሄድ እየተጠበቀች መሆንዋ ቅድስነታቸው ለብፁዓን ጳጳሳቱ መግለጣቸው የቫቲካን መግለጫ አመልክተዋል።

ቅዱስ ኣአባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጣልያን ብፁዓን ጳጳሳት ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ እንደገለጹት ፡ መንፈሳዊ ቀውሶች ወደ ጐን ትቶ ለኤኮኖምያዊ ቀውሶች መፍትሔ ማግኘት ማሰብ ፡ ስህተት ነው ።

ስብከተ ቅዱስ ወንጌልን ዳግም ለመቀስቀስ በሚደረግበት ግዜ የቤተክርስትያን አባላት ተዳክመው ሐጢአት በመፈጸማቸው በርሷ ላይ የተከሰቱ ቁስሎች ተደብቀው አይቀሩም ፡

ይህ ስለሆነ ግን ቤተክርስትያን ለምእመናን የምትሰጠው ሐዋርያዊ አገልግሎት መደናቀፍ የለበትም በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለጣልያን ጳጵሳት መግለጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስገንዝበዋል።

በውሁዳን የቤተክርስትያን አባላት የተፈጸሙ ሐጢአቶች ንስሐ ጸለሎት እና ንጽህና በማዘውተር መቋቋም እና አዎንታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚያሻ አያይዘው መገልጣቸው ተመልክተዋል።

አለ ንስሐ ንጽህና አይገኝም ያላኡት ቅዱስ ኣአባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በአጠቃላይ የቤተክርስትያን አባላት ለንስሐ እና ለጸሎት መጋበዛቸውን ተያይዞ ተነግረዋል።

የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር እና የጀኖቫ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለጳጳሳቱ የሰጡትን አባታዊ ምክር ማመስገናቸው እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቤተክርስትያን ከሄሉ ኩሉ እግዚአብሔ እንድትሆን እንደፈለጋት ዓይነት ሆና እንድትገኝ እና ቅርቡ እንድትሆን እያካሄዱት ያሉትን ሐዋርያዊ ሙያ የጣልያን ጳጳሳት አጋርዎ ይሆናሉ በማለት መግለጣቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.