2010-05-28 13:59:41

እውቅና ለዓለም ዓቀፍ የአያው ፍርድ ቤት


አምነስት ኢንተርናሽናል በመባል የሚጠራው ዓለም አቀፍ የሰውብአዊ መብት ተሟጋች ማኅበር ዓለም አቀፍ ፍትህ የሁሉም ፍላጎት መሆኑ በአለማችን ያለው የሕግ እና ፍትህ ጉዳይ በመዳሰስብ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በማስደገፍ RealAudioMP3 ባጠናቀረው የ 2010 ዓ.ም. ሰነድ አማካኝነት፣ በጠቅላላ ሁሉም አገሮች አንድም ሳይቀር ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እውቅናን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በብዙ አገሮች አሁንም የፍትህ እጦት የፍርድ ቤት ችሎት መጓተተ፣ ፍትሕ እና ፖለቲካ በማጣመር ፍትህ በሥርዓተ መንግሥታት ሥር በማኖር የሚያስተላልፈው ውሳኔ መሠረት የሚተላለፈው ኢፍትኅዊ ፍርድ በአለማችን የሚሰቃየው ሕዝብ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ ሰንዱ ሲያመለክት፣ አመጽ፣ አድልዎ ዘረኝነት የመሳሰሉት ጸረ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚታይባቸው አገሮች እንዳሉም ለማወቅ ሲቻል፣ ገና 81 ኣገሮች ለአያው ፍርድ ቤት እውቅናን አለ መስጠታቸው ሰነዱ ይጠቁማል።

ከእነዚ አገሮች ውስጥ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እና ሩሲያ እንዲሁም ህንድ ኢንዶነዢያ ሳውዲ አረቢያ እና ቱርክ ለመጥቀስ እንደሚቻል የአምነስት ኢንተርናሽናል ሊቀ መንበር ክሪስቲነ ዋይሰ ሰነዱን በማስደገፍ በሰጡት መግለጫ በማብራራት እ.ኤ.አ. 2009 ዓ.ም. በአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ ዓለም አቀፍ የሕግ እና ፍትሕ ከፍተኛ መቃወስ የታየበት ዓመት እንደነበርም ዋይሰ በማስታወስ፣ በዚህ በያዝነው 2010 ዓ.ም. መሻሻል መታየቱ የማይካድ ነው ካሉ በኋላ ማንም አገርም ይሁን መንግሥት ከሕግ እና ፍትህ በላይ ሊሆን አይችልም፣ ስለዚህ የሰው ልጅ መብት እና ፈቃድ አለ ምንም ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊ ባህላዊ ወዘተረፈ ቅድመ ሁኔታ መከበር አለበት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.