2010-05-28 13:56:56

እምነት እና ስሥቃ


የጀኖቫ ትልቁ መንበረ ጥበብ ከሮማ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ ጋር በመተባበር ኅመም እና ሃይማኖት ጥንት እና አሁን በሚል ርእስ ሥር የተመራ ሮማ በሚገኘው ቅዱስ መንፈስ የህክምና ማእከል በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ RealAudioMP3 በመካሄድ ላይ ባለው አውደ ጥናት የተገኙት የጤና ጥበቃ እና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጉዳይ ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዚሞውስኪ ስቃይ እና እምነት በሚል ርእስ ሥር ሰፊ አስተምህሮ ማቅረባቸው ተገለጠ።

ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ቤተ ክርስትያን ክርስቶስ ስለኛ ብሎ መሰቃየቱ እና ስቃዩም የድህነት ምልክት እና ማረጋገጫ መሆኑ ታሰተምራለች፣ ስለዚህ መዳናችን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም ጋር የተቆራኘ ነው። ክርስቶስ በመሰቃየት ስቃይን ጭምር አድነዋል፣ የሰው ልጅ ስቃይ በክርስቶስ ስቃይ የዳነ ስቃይ ነው። ለሚሰቃየው ቅርብ መሆኑ፣ ስቃዩ እንደማይመለከትህ እና ከራስህ ገጠመኝ አንጻር በመመልከት ለታመመው ምን ልርዳህ ሳይሆን የስቃዩ ተካፋይ መሆን ያስፈልጋል። የአንዱ ሕመም የኔ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በወቅቱ ባለ መታመሜ ምክንያት የስቃይ ተካፋይ ከመሆን መሸሽ የለብኝም፣ በያንዳንዱ የሰው ልጅ የመታመም እምቅ ግፊት አለ፣ ክርስቶስ ይኸንን ስቃይ ጭምር የራሱ በማድረግ ስቃያችንን ከእኛ በላይ የራሱ በማድረግ ስቃያችንን አድነዋል፣ ስለዚህ ለኅመምተኞች የሚሰጠው አገልግሎት ምን ዓይነት አገልግሎት መሆን እንዳለበት ለመገመቱ እያዳግትም ብለዋል።

ሕክምና ከአሌ ኵሉ ሊሆን አይችልም፣ ሆኖም እያውቅም፣ ስለዚህ ሕክምና ሕመምተኛውን የሚደግፍ እና ከአንዳንድ በሽታ የሚፈውስ እንጂ የአለ ታማሚነት ኃይል አያሰጠንም በሽታን ጨርሶ ከምድረ ገጽ ዓለም አያጠፋም፣ በሽተኛው መደገፍ ማለት በሽታውን መደገፍ ማለት አይደለም፣ መመሪያው ይህ ሊሆን እየተገባው፣ የህክምናው ጥበብ ምርምር በሽታን ለመፈውስ በሽታው ከሚሸከመው ሰው ውጭ በመምልከት ትኵረታቸው በበሽታው ላይ ብቻ ሲያደርጉ ይታያል፣ ቤተ ክርስትያን ከዚህ አንጻር የስነ ሕክምና ዓላማ ምን መሆን እንዳለበት በማሳሰብ፣ የታመመውን በመደገፍ በእምነት በማጽናናት፣ ብዙውን ጊዜ የታመመው የሚያቀርበው እርሱም ለምን እኔ የሚለው የስነ ኅልውና ጥያቄ መልሱ ከእምነት መሆኑ ታስተምራለች ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.