2010-05-28 13:55:21

ብፁዕ አቡነ ራቫዚ፣ ከኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስትያን የሚደረገው ውይይት እንዲበረታ


የእግዚአብሔር ቃል በሚል ርእሥ ተመርቶ የተካሄደው የመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ውጤት መሠረት የዩክራይን ሃይማኖታዊ ባህላዊ ገጽታውን ለማንበብ እና በዚህ መሠረትም ክብሩን ለማድመቅ ከኦርቶዶክ RealAudioMP3 ስ ቤተ ክርስትያን ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት እና ግብረ ኖልዎ ለማጠከር ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፅዕ አቡነ ጃፍራንኮ ራቫዚ በዩክራይን ሓውርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አረጋገጠ።

የእግዚአብሔር ቃል በቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው የመላ ካቶሊክ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ በኡክራይን ወቅታዊው ሁኔታ ሥር በማንበብ የእግዚአብሔር ቃል በዩክራይን ሕይወት እና ቤተ ክርስትያን በሚል መሪ ሃሳብ የተመራ ሓዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ሲገለጥ፣ ብፁዕ አቡነ ራቫዚ በኪየቭ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ሥር የምትመራው የኡክራይን ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን ሜትሮፓሊታ ቭላድሚር ጋር እንደሚገናኙም ተገልጠዋል።

ይህ ሓዋርያዊ ጉብኝት የኤውሮጳ ሥልጣኔ መሠረት የሆነው የእግዚብሔር ቃል ማለትም ቅዱስ መጽሓፍ ዳግም ኅያው ለማድረግ እና የኤውሮጳ ኅብረሰብ ክብር እንዲሰጠው ለማነቃቃት የእግዚአብሔር ቃል ማእከል ያደረገ ሓዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ቀደም በማድረግ አሳውቀው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን። ጉብኝቱ ከዩክራይን ባህል ኅብረተሰብ እና የአቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት ለማጎልበት የሚል አድማስ ያለው ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ፣ የጋራው ውይይት ካለው ልዩነት አንጻር የሚከናወን ነው። ውይይት ማለት ልዩነትንም ጭምር ያሰማል፣ ስለዚህ ውይይት ስምምነትን ብቻ አያመለከትም የውኅደ ሙዚቃ ሂደት ያለው ነው። ሆኖም ከዚህ ልዩነት የተሟላ ውህደት ያለው ጣፋጭ ሙዚቃ ይደመጥ ዘንድ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን አቢይ ጥረት እንደሚጠይቅ ያመነ ሓዋርያዊ ጉብኝት ነው እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.