2010-05-28 13:54:22

ስሜተ ጵጵስና በእየሩሳሌም


በእስራኤል እየሩሳሌም ከተማ የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ለካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ረዳት እዲሆኑ እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተመረጡት ኣባ ዊሊያም ሃና ሾማሊ ትላንትና RealAudioMP3 በፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ስሜተ ጵጵስና ተፈጽሞላቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ሾማሊ በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን ድረ ገጽ በኵል በሰጡት መግለጫ፣ በዚህ የእረኝነት ተልእኮአቸው የሚጠብቃቸው አቢይ ኃላፊነት በቅድስት መሬት ካለው አስቸጋሪ ሁኔታ በመነሳት የሚጋፈጥዋቸው እክሎች በመጥቀስ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውም ሲገለጥ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እጅግ የተወጠረ እርሱም ይኸው ዘመን እያስቆጠረ ያለው በክልሉ ያለው ውጥረት በወታደራዊ ኃይል የተሸኘው ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ክልላዊ ፖለቲካዊ እና የርእዮት ባህይር ያለው መሆኑ ገልጠው፣ በክልሉ ያለው ግጭት የሚፈታው ብቸኛው የሰላም መንገድ የሆነው የውይይት መድረክ መነቃቃት ያለበት ጉዳይ ነው፣ አመጽ ጨርሶ መፍትሔ ሆኖ አያውቀም፣ ስለዚህ ትእግሥት የተካነው ውይይት በጋራ በመሥራት እና ከአሌ ኵሉ የሆነው እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲሰጠን መጸለይ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ነገ ከነገ ወዲያ ባይሆንም ሰላም የሚረጋገጥበት እለት አይቀሬ ነው። የእግዚአብሔር የሰዓት አቆጣጠር ከእኛ የተለየ ነው፣ በትጋት በትእሥት ተስፋን በማስቀደም መጸለይ ይኖርብናል ካሉ በኋላ የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ለስደት የተጋለጠ መሆኑም በመጥቀስ፣ በስደት የሚኖረው የመካከለኛው ምሥራቅ ክርስትያን ማኅበረሰብ በመካከለኛው ምሥራቅ ካለው ክርስትያን ማኅበረሰብ በቁጥር እጅግ ከፍ ያለ ነው በማለት፣ በቺለ 3 መቶ ሺሕ ፍልስጥኤማውያን ክርስትያኖች እንዳሉ ገልጠው፣ በዚህ ክልል የተመዛዘነ አመለካከት ያለው ማኅበረሰብ የክርስትና እምነት ተከታይ መኖኑ በማብራራት፣ በክልሉ የክርስትያኖች ኅልውና ከዚህ አንጻር ብቻ ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ ለመገንዘብ አያዳግትም፣ አይሁዳውያንም ሆኑ ሙስሊሞች በክልሉ የማኅበረ ክርስትያን ኅላዌ ለሰላሙ ሂደት እጅግ አስፈላጊ እና የክክሉ ሁኔታ ሚዛኑ እንዲጠብቅ የማድረግ ብቃት ያለው ማኅበረሰብ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ሾማሊ አብራርተዋል።

ስለዚህ በዚህ ክልል የክርትያኖች ኅላዌ ዕጣ ዕድል ሳይሆን ቡራኬ ልዩ ተልእኮ እና ጥሪም ጭምር መሆኑ ማሳመን የክልሉ ቤተ ክርስትያን አቢይ ኃላፊነት ነው ብለዋል። እግዚአብሔር በዚህ ክልል እንድንኖር የጠራን ክርስትያኖች የክልሉ ዜጎች ሆነን እያለን፣ አናሳው የክልሉ ማኅበርሰብ በመሆናችንም ይላሉ በቁምስና በክልሉ በሃይማኖታዊ እና በባህል ረገድ ተለይተን ተነጥለን እንድንኖር የሚገፋፉ ብዙ ፈተናዎች ቢያጋጥመንም ከዚህ አጥራዊ ኑሮ ተገለን ልክ እንደ ሓዋርያት መንፈስ ቅዱስ ተቀብለው ታጥረውበት ከነበረው የፍራት እና የጭምንቀት ቤት ተላቀው ተበራትተው ምንም እንኳ በቁጥር አናሳ የነበሩ ቢሆንም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተልእኮ ለሁሉም ለማዳረስ ችለዋል። ስለዚህ ከታጠርንበት ክልል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልተን መውጣት ይኖርብናል ብለዋል።

በመጨረሻም በመካከለኛው ምሥራቅ ያላችው ካቶሊክ ቤተ ክርስይታን ከእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አቢይ ድጋፍ እንደምታገኝ በመጥቀስ እግዚኣብሔር ጥበቃውን እና አሳቢነቱን አልነሳንም በማለት፣ በዚህ አጋጣሚ በመካከለኛው ምሥራቅ ለምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ደገፍ ለሚያቀርቡት እና ቅርበታቸውን ለሚገልጡት በተለይ ደግሞ ዘወትር በጸሎታቸው ለሚያስቡአቸው እና ምክራቸው እና መሪ ቃላቸውን ለሚለግስግሱት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምስጋናን በማቅረብ የአቢያተ ክርስትያን መከፋፈል ተወግዶ ክርስቶስ የጸለው ውህደት እንዲረጋገጥ ስለ ሁሉም ክርስትያኖች ውህደት መጸለይ አለብን ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.