2010-05-26 13:29:28

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


ከትላትና በስትያ በቫቲካን የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይፋዊ ጉባኤ በምክር ቤቱ ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባሰሙት ንግግር መጀመሩ ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ኢጣሊያ በወሊድ ቁጥር ማነስ ምክንያት RealAudioMP3 እራስን የመግደሉ ድርጊት እያረማመደች መሆኗ በማብራራት፣ የማንም ኅብረተሰብ መሠረት የሆኑን ቤተሰብ እና ሥራ ለማነቃቃት የሚችል ብቃት ያለው ፖለትካ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ስለዚህ ቤተ ሰብ ድጋፍ እና ኤኮኖምያዊ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ዋስትና ካልተረጋገጠለት ያንድ ኅብረተሰብ ኅልውና አስተማማኝነቱ ያጠራጥራል በማለት፣ አክለውም በኢጣሊያ ያለውን የፖለቲካው መድረክ በተመለከተ ኢጣሊያ ያለባት ችግር ተቀዳሚ ርእስ በማድረግ መፍትሔ እንዲያገኝ በመምራት ላይ ያለው እና ተቃዋሚው የፖለቲካ ሰልፍ ላለ መስማማት ከማሰቡ ፈተና ተላቀው በሳል ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ንግግራቸውን በመቀጠል፣ የኢጣሊያ ከመከፋፈሉ ታሪክ ተላቃ አንድነትዋን ካረጋገጠች ይኸው 150ኛው ዓመት እየተዘከረ መሆኑም አስታውሰው፣ በዚህ የአንድነት ታሪክ ካቶሊክ ምእመናን የሰጡት አስተዋጽኦ የፖለቲካው መድረክ ሊዘነጋው አይገባም ብለዋል።

የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ለኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያስተላለፉት መልክት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በመጥቀስ፣ ለኢጣሊያ ውህደት እና አንድነት እንዲሁም ለማኅበራዊ እድገት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን የከፈሉት ወደር የማይገኝለት አቢይ አስተዋጽኦ ዘክረው፣ በኢጣሊያ ታሪክ መቼም ቢሆን የማይሻር የታሪክ ሓቀኛ ትውስት ሆኖ እንደሚቀር ማረጋገጣቸው ከገለጡ በኋላ በአሁኑ ወቅት ገሃድ እየወጣ ያለው አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የፈጸሙት አመጽ በመጥቀስ ቤተ ክርስትያን ምንኛ እንደተሰቃየች በማብራራት የአመጹ ሰለባ የሆኑትን በማስታወስ የስቃያቸው ተካፋይ መሆኗ በማረጋገጥ የተሟላ ደገፍ እንደምታቀርብ ገልጠው፣ የውሉደ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት እንዴት መካሄድ እንዳለበት ማለትም መንፈሳዊ ስነ አእምሮአዊ፣ ሰብአዊ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ሕንጸት ምን እና እንዴት መሆን እንዳለበት በጥልቅ ያስገነዘበ ጉዳይ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.