2010-05-26 13:28:24

የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት


እስከ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚካሄደው የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት 19ኛው ይፋዊ ጉባኤ ዛሬ በይፋ መጀመሩ ከቅድስት መንበር የተላለፈ RealAudioMP3 መግለጫ ያመለክታል።

ጉባኤው ብፁዓን ካርዲናላት ብፁዓን አቡናት እና ካህናት በጠቅላላ 23 የምክር ቤቱ አባላት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ 10 የምክር ቤቱ የመማክርት አባላት ያሳተፈ፣ በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚታየው የሰዎች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሂደት እግምት ውስት ያስገባ የሚቀርበው ሓዋርያዊ አገልግሎት እና የመንግሥታት እና የአለም አቀፍ ማኅበራት ኃላፊነት በሚል ርእስ ሥር የተመራም እንደሚሆን ይፋዊ መግለጫ የሰጡት የስደተኞች እና የተጓዦች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ ቀደም በማድረግ አስታውቀው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በስብሰባው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ተራድኦ ማኅበራት እና መንግሥታዊ ያልሆኑት ዓለም አቀፍ የግብረ ሰናይ ማኅበራት ተጠሪዎች ጭምር እየተሳተፉ ናቸው።

ሃብታም አገሮች ከእስያ እና ከእፍሪቃ ስደተኞች የሚያገኙት የሥራ ጉልበት በሚል ርእስ ሥር ዛሬ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የስደተኞች እና የተጓዦች ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ፣ ዓለማችን እያረጀ ነው፣ የህዝብ ብዛት ዝቅ እያለ በመሆኑም፣ ይህ ክስተት ህዝቦች ከቦታ ቦታ እንዲዘዋወሩ እያስገደደ ነው። በበለጸገው ዓለም የሚታየው የወሊድ ቁጥር ማነስ ምክንያት የበለጸገው ዓለም የሚከተለው የልማት እቅድ ዋስትና ለመስጠት እያዳገተው በመሆኑ፣ የሚያስፈልገው የሰው-ሠራተኛ-ኃይል ከደቡቡ የዓለማችን ክፍል በተለይ ከእስያ እና ከአፍሪቃ መፍትሄ እያገኘበት ነው።

የወሊድ ቁጥር ማነስ የአምራቹ ኃይል እንዲጎድል የሚያደርግ ሲሆን፣ ከወጣቱ ብዛት እና ከሠራተኛው ብዛት ይልቅ የጡረተኛው ሕዝብ ብዛት ከፍ እያለ በመምጣቱ ምክንያት በኃብታም አገሮች የኤኮኖሚ መቃወስ እያስከተለ ነው፣ ስለዚህ የአምራቹ ብዛት የጡረተኛው ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የጡረታ አበል፣ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ወጪ ለመሸፈን እያዳገተው በመሆኑም የልማቱ ሂደት ላይ ጭንቀት እያሳደረ መጥተዋል። የነዳጅ አምራች አገሮች የነዳጅ ሃብት ያለውን እምንቁን የኤኮኖሚ ሃብት እጥቅም ላይ ለማዋል ከድኾች አገሮች በሠራተኛ ውል ውሳኔ ስደተኞች በማስገባት፣ ምጣኔ ኃብታቸው ካላቸው የተፈጥሮ ሃብት ጋር እንዲመጣጠን በማድርጉ ሂደት ሲጣደፉ ይታያል፣ እውነቱ ይኽ ሆኖ እያለ በኤውሮጳ እና በሰሜን አመሪካ የስደተኛው ሥራ የማግኘት እድል እጅግ የመነመነ ሆኖ ማየቱ የሚገርም ነው።

የስደተኛው የሙያ ሕንጸት ደረጃ በሚስተናገድበት አገር ከሚሰጠው ሕንጸት ጋር የማይመጣጠን ሆኖ ሊገኝ ይችላል፣ ይህ በመሆኑ ደግሞ በስደት በሚኖርበት አገር ስደተኛው ተፈላጊነቱ ከፍ ያለ ሆኖ እያለ ነገር ግን የተሟላ ሕንጸት እንዲያገኝ እድሉ አይፈጠርለትም፣ ከዚህ ጋር በማያያዝ የባህል የሃይማኖት ልዩነት ተጨምሮበት ተገሎ እንዲኖር ይገደዳል፣ ስለዚህ ይህ ሁሉ ችግር ለመፍታት የውህደት መርሃ ግብር ማፋጠን እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት የሚታየው የአሸባሪያን ኃይሎች ሴራ እና አንዳንድ ስደተኞች የሚፈጽሙት ወንጀል ከምዕራቡ ዓለም ማንኛውም ዜጋ ከሚፍፈጽመው ጋር የሚመሳስል ሆኖ እያለ ብዙውን ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን እጅግ በማጋነን በስደተኛ ብቻ የሚፈጸም የሚያስመስለው የሚያቀርቡት ዜና ብሔራው የጸጥታ እና የደህንነት አንገብጋቢ ጥያቄ እንዲሆን አስገድደዋል፣ ይህ ጉዳይ በስደተኛው ላይ አቢይ ችግር እያስከተለ ነው፣ በስደተኛው ላይ ጅምላዊ ፍርድ በመስጠት ገና ከወዲሁ ወንጀል እና ስደተኛ በማመሳስል ለአገር ጸጥታ እና ደህንነት በሚል ሰበብ ብዙ አገሮች ድንበራቸው በመዝጋት የመቆጣጠሩ ሂደት በማሳየል፣ በስደተኛ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እጅግ ከባድ እየሆነ መጥተዋል። ቤተ ክርስትያን በዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ ለሚገኘው ስደተኛ ቀርባ በምተሰጠው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተሟላ ሕንጸት በማቅረብ ላይ እንደምትገኝ በማብራራትም፣ ስደተኛው ለባህል ለኅብረተሰብ ሃብት መሆኑ የሚያብራራ ስድተኛው የተስተናገደበት አገር ጋር እንዲተዋወቅ እና ስደተኛው ለተስተናገደበት አገር ሕዝብ ጭምር ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ታቀርባለች እንዳሉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.