2010-05-26 14:05:46

የር.ሊ.ጳ. የዕለተ ሮቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አጠቃላይ አስተምህሮ 26.05.2010


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጲጥሮስ አደባባይ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው፣ ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ10 “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። እኔና አብ አንድ ነን”።የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው በሰፊው የዛሬን ትምህርተ ክርስቶስ በጣልያንኛ ቋንቋ አቅርበዋል፣ የሚከተለውንም በእንግሊዘኛ በአጭሩ አስተምረዋል፦ “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦ በዚሁ የክህነት ዓመት መጨረሻ ቀናት ስለ ካህን በክርስቶስ ስምና ሥልጣን ለእርሱ አደራ የተሰጡት በጎች የማስተዳደር ተልእኮ መናገር እወዳለሁ፡ ሥልጣን በክርስትና አስተሳሰብ የሰው ልጆች የመጨረሻ መልካም ግብ የሆነው ማለትም በኢየሱስ ጌታ ስም ዘለዓለማዊ ደህንነት የሚደረግ እውነተኛ አገልግሎት ነው። ይህም የመልካሙ እረኛ ስለበጎቹ አሳቢነትና በመህከላቸው ዘወትር የመኖር መግለጫ ነው፡ ካህን በመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ የተቀበለውን መንፈሳዊ ሥልጣን በልቡ በመታመንና የክርስቶስ መሪነትን በቅድምያ ለመታዘዝ ራሱን በመዘጋጀት ማስተካከል አለበት፡

በእምነት ብርሃን እንደምንረዳው ይህ መዓርግ ሥልጣንን ሲያለብስ ገና ቤተ ክርስትያንን በቅድስና በአንድነትና በእውነት የማነጽ አገልግሎትን ይጠይቃል፡ የክርስቶስ ሥልጣን የሐዋርያት እግር በማጠብ ተገለጠ። የክርስቶስ ንግሥነት በእንጨት መስቀል ላይ በመንጠልጠል ታወጀ። የማስተዳደር ክህነታዊ ተልእኮም በፍቅር ግብረ ተልእኮ እተግባር ላይ መዋል አለበት፡

ሁላችሁ ካህናቶቻችሁን ለወንጌል ሕቅና ለመልእክቱ ተስፋ በመመስከር  የእግዚአብሔር ልጆች ለመምራት በሚያቀርቡት ተልእኮ እንድትደግፍዋቸው አደራ እላለሁ። በተለይም ለቤተ ክርስትያን የማቀርበው የአስተዳደር ተልእኮየ የተሳካ እንዲሆን ለእኔ እንድትጸልዩልኝ እማጠናለሁ። እንዲሁም የምናከብረው የክህነት ዓመት መንፈሳዊ ፍሬ እንዲሰጥ ጸልዩ፡ ብለው በመማጠን ትምህርታቸውን ለመስማትና ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ለመቀበል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች አመግነዋል፡።








All the contents on this site are copyrighted ©.