2010-05-26 17:40:03

በዒራቅ አዲስ ሊቀ ጳጳስ ፡


በዒራቅ የካልደይ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ባሻር ቫርዳ የአርቢል ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ባለፈ ቅርብ ግዜ እንደሰየማቸው እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ስያሜው ማጽደቃቸው የሚታወስ ነው።

በዒራቅ የአርቢል አዲሱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባሻር ቫርዳ የዒራቅ ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው መግለጫ ሲሰጡ እንዳመለከቱት ፡ የዒራቅ ቤተ ክርስትያን ልክ የቅዱሳን ወንጌላውያን ዕድመ ቢናራትም ቅሉ ራስዋ በማነጽ ላይ ትገኛለች። ለምን ቢባል ይላሉ የአርቢል አዲስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባሻር ቫርዳ ባለፉት ዓመታት ሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ክርስትያኖች ላይ የጥቃት እና የማሳደድ ርማጃ በመወሰዱ መሆኑ መግለጣቸው ተዘግበዋል።

ይሁን እንጂ በዒራቅ የካልደይ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በእምነት የገጠምዋትን ችግሮች ሁሉ ለመወጣት ያለሰለሰ ጥረት እያካሄደች መሆንዋ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባሻር ቫርዳ ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

ብፅዕነታቸው እንደገለጡት በዒራቅ የአርቢል ሀገረ ስብከት እኤአ በ2005 2.500 ካቶሊካውያን አቀፍ መኖርዋ ጠቅሰው አሁነ ከርእሰ ከተማ ባቅዳድ እና ከሞሱል ሸሽተው የመጡ ክርትስትያን ቤተ ሰቦች ጨምሮ 7.200 ቤተሰበኦች ብቻ ይዛ መቅረትዋ በሐዘን ገልጸዋል።

ዒራቅ ውስጥ በክርስትያኖች ላይ የተነሳው የማጥቃት እና የማሳደደ ተግባር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ክርስትያኖች ሀገሪቱ ለቀው ወደ ተጓራባች ሀገራት ወደ ሲርያ ሊባኖስ እና ዮርዳኖስ መሰደዳቸው አያይዘው አስረድተዋል ።

የአርቢል አዲስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባሻር ቫርዳ ባለፉት ዓመታት በርካታ ክርስትያኖች በግፍ መገደላቸው ለእስር መዳረጋቸው የሚዘነጋ እንዳልሆነም አመልክተዋል።

አሁንም ቢሆን የዒራቅ ሁኔታ የረጋጋ እና የክርስትያን ማኅበ ረሰቦች ጸጥታ የተጠበቀ እንዳልሆነ በማመልከት ፡ ቤተክርስትያኒቱ የቤተክርስትያን ትምህርት መሰጠት እንደምትቀጥል እና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ማኅበረ ሰቦች በትምህርት እና በጤና ጥበቃ በኩል በመተባበር እንደምትሰራ ገልጠዋል።

የዒራቅ ቤተክርስትያን በማኅበራዊ ዘርፎች በኩል ከኅብረተ ሰቡ ጋር በመተባበር ምስራት እና ለወጣቶች የተሻለ መፃኢ ዕድል ማፈላለግ እንደሚጠበቅባት ያመልከቱ በIራቅ የአርቢል ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ወንጌል ተልእኮ እና የቤተ ክርስትያን ማሕበራዊ ትምህርት በበለጠ የምትሰራበት ግዜ መሆኑ አስረድተዋል።

ሀገሪቱ ውስጥ በተከሰተው አስከፊ ሁኔታ የተሰደዱ ክርስትያኖች ወደ ሀገራቸው የሚመለሱም ቤተክርስትያን ጠንክራ ከሰራች እና ተስፋ ሰጪ እቅዶችን በማውጣት ለገቢራውነታቸው ከሰራች እንደሆነ መሆኑም የአርቢል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ባሻር ቫርዳ አያይዘው ማስረዳታቸው ታውቆዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.