2010-05-26 17:37:23

በቅድስት መንበር እና ሃንዛ ስቴት ሃምቡርግ መካካል ስምምነት ተፈርመዋል፡


ባለፈው ቅርብ ግዜ ቅድስት መንበር እና በሰሜናዊ ጀርመን የሃምበርግ ሃንዛ ነጻ ከተማ ከተማይቱ ላይ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ የሥነ ትምህርት የካቶሊክ ንባበ መለኮት ማእከል እንዲከፈት ተስማምተው መፈራረማቸው የቫቲካን መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ ሃምበርግ ላይ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈረመው ስምምነት በቅድስት መንበር በጀርመን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጂን ክላውደ ፐሪሰት

በሃምበርግ በኩል በሃገሪቱ ሴነት የሳይንስ እና የምርምር የበላይ ሐላፊ ወይዘሮ ሄርሊንድ ጉንደላኽ መፈረማቸው መግለጫው አስታውቀዋል።

በዚሁ በሰሜናዊ ጀርመን በሃምበርግ ሃንዛ ነጻ አስተዳደር በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ የሥነ ትምህርት ካቶሊካዊ ማእከል እንደከፈት የተደረገው ስምምነት ፡ የሃምበርግ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቨርነር ቲሰን ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሃንስ ዮኸን ያሽከ የዩኒቨርሲቲው ፕረስዳንት ፕሮፈሶር ሆልገር ፊሸር እና በርካታ ጥሪ የተደረላቸው እንግዶች መገኘታቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.