2010-05-26 13:27:16

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ኢየሱስን በእምነተ አይን እንመለከተው ዘንድ


ግንቦት የማርያም ወር ተብሎ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን በየዓመቱ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን የማርያም እምነት የሚስተነተንበት ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንደሚያስታውሱን እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ከማርያም ጋር RealAudioMP3 የምንኖርበት ወር ነው። ይህ የማርያም ወር እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቫቲካን በሚገኘው አጸድ በሚመሩት ማርያማዊ ጸሎት እንደሚጠናቀቅም ከውዲሁ ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን የማርያም እምነት፣ ለሁሉም ክርስትያን አብነት በተሰኘው ርእስ በሰጡት ጥልቅ አስተንትኖ፣ ማርያም መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ኅያው መሆኑ እርሱም ሕይወታችን በክርስቶስ ሙላት እንዲያድግ ታስተምረናለች። ከማይወላወለው እና ከማይጠራጠረው የማርያም እምነት እንድማር ቅዱስ አባታችን አደራ በማለት፣ ማርያም በታሪክ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች በእምነት ዓይን ቀርባ በመመልከት እና በማመን፣ ያቀረበቸው የምስጋና ጸሎት ታሪክን የሚተነትን ልዩ፣ ተምሳይ የሌለው እውነተኛ እና ጥልቅ ጸሎት ነው። የማርያም የምስጋና ጸሎት ታሪክን የሚዳስስ ታሪክን የሚፈታ እና የሚያብራራ እውነተኛው ሂደቱን የሚገልጥ መሆኑ በማብራራት እያንዳንዱ ክርስትያን ይኸንን ማኚፊካት እርሱም የማርያም የምስጋና ጸሎት በልቡ አቅቦ ይኖረው ዘንድ እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2008 ዓ.ም. የማርያም ወር መዝጊያ ባቀረቡት አስተምህሮ አደራ እንዳሉ የሚታወስ ነው።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2009 ዓ.ም. የማርያም ወር ለመዝጊያ የተካሄደው መንፈሳዊ ሥርዓት በምምራት የማርያም ልብ የመንፈስ ቅዱስ እውነት ማደሪያ የእግዚአብሔር ቃል እና ድርጊት በእምነት በተስፋ እና በፍቅር የሚታቀብበት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ፍጹም ውህደት ሥፍራ ነው በማለት፣ ማርያም መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ሙሽሪት፣ በክርስቶስ እምነት በማኖር በእምነት ከእምነት በእግዚአብሔር ዳግም ለሚፈጠሩት እናት መሆኗ፣ እርሱም የማርያም እናትነት፣ ኵላዊ ገጽታው የተገለጠበት መሆኑም አብራርተው፣ ለዚህም ነው ማርያም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የክርስቶስን ዳግም መምጣት የምትጠባበቀው ቤተ ርክስትያን እና የሚጠባበቀው ለሁሉም የሰው ዘር አርአያ እና አብነት የሆነችው፣ በማለት አስተምረዋል።

ማርያም ኢየሱስን በማህጸንዋ በመቀበል ወደ ሌሎች በማድረስ እውነተኛውን የክርስትያን ደስታ ምን መሆኑ መስክራለች፣ ወድ ወድሞቼ እና እህቶቼ የማርያምን ዱካ እንከተል፣ የማርያም መንፈስ ጥልቅ ቅዱስ ቁርባናዊ አድማስ ያለው መሆኑ እርሷን እንምሰል በማለትም እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2005 ዓ.ም ለማርያም ወር መዝጊያ ባቀረቡት አስተምህሮ ተመልክቶ ይገኛል።








All the contents on this site are copyrighted ©.