2010-05-25 13:30:03

የቅዱስ ቄርሎስ እና መቶዲዮስ ክብረ በዓል


የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ታህሳስ 31 ቀን 1980 ዓ.ም. ባስተላለፉት ሓዋርያዊ መልእክት መሠረት ቄርሎስ እና መቶዲዮስ ከቅዱስ በነዲክቶስ ዘ ኖርቺያ ጋር የኤውሮጳ ጠባቂ ቅዱሳን እንዲሁኑ መወሰናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ባለፈው ቅዳሜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የእነዚህ የኤውሮጳ ጠባቂ ቅዱሳት በዓል ምክንያት የቡልጋሪያ እና የመቄዶኒያ መንግሥታት ልኡካን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ቅዱስ አባታችን የቡልጋሪያ መራሄ መንግሥት ቦይኮ ቦሪሶቭ ቀጥለውም የመቄዶኒያ ትራጃኮ ቨልዣኖስኪን በመቀበል ባሰሙት ንግግር፣ በኤውሮጳ ከቅዱሳት ቄርሎስ እና ሜቶዲዮስ የላቀው ክርስትያናዊ ትምህርት የመነጨው ክርስትያናዊ መሠረት ማነቃቃት እና መመስከር አስፈላጊ ነው ብለዋል። እነዚህ ወንድማማቾች የተሰሎንቄ ዜጎች የሰጡት ክርስትያና አብነት እና ያቀረቡት ስብከተ ወንጌል ለኦርቶዶክስ እና ለካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ዘንድ የጋራ ክርስትያናዊ ሃብት መሆኑም በማብራራት ለዚህ ክርስትያናዊ ትምህርት ታማኝ እና በቅናት ማቀብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የወንጌል እሴቶች በኤውሮጳ እንዲስፋፋ እና በእያንዳንዱ የኤውሮጳ ዜጋ እንዲታወቅ እና በልብ እንዲሰርጽ ያደረጉ የኤውሮጳ ባህል ክርስትያናዊ መሠረት ያለው መሆኑ የሚመሰክር ነው። ስለዚህ ይህ ክርስትያናዊ ባህል ማቀብ እና መመስከር የሁሉም የኤውሮጳ ዜጎች እና አገሮች ግዴታ ነው ብለዋል። ብዙ ስቃይ እና መከራ ያሳለፉት ቅዱሳት ቀርሎስ እና ሜቶዲዮስ በእግዚአብሔር ላይ የማይናወጥ እምነት እና የማይሸነፍ ተስፋ በማኖር ወንጌል የመሰከሩ መሆናቸውም ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፣ ሁሉም የኤውሮጳ ዜጋ የዚህ ክርትያናዊ ሃብት ተቀባይ ነው በማለት መንፈስ ቅዱስ በሚሰጠው በተለያየው ስጦታ አማካኝነት ፍቅር መኖር እና ማገልገል አለብን በክርስትያናዊ ጉዞ ስንደክም መንፈስ ቅዱስ ፈጣን ረዳታችን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.