2010-05-25 13:28:07

በዓለ ጰራቅሊጦስ፣ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ያለን የእምነት ምስክርነት


በላቲን ሥርዓት ትላትና ስለ ተከበረው በዓለ ጰራቅሊጦስ ምክንያት በኢጣሊያ የክሮቶነ እና የሳንታ ሰቨሪና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒኮ ግራዚያኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓለ ጰራቅሊጦስ የቅድስት ሥላሴ ሶስተኛው አካል በዓል መሆኑ በማብራራት፣ በዓሉ በዚህ ሶስተኛው የቅድስት ሥላሴ አካል ላይ ያለን እምነት የምንመሰክርበት እለት ነው ብለዋል።

ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ነጻነት ደስታ እራስን መቆጣጠር ሰላም መረጋጋት በጠቅላላ እያንዳንዱ ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበለውን ጸጋ ለራስ እና ለማኅበራዊ ጥቅም በማዋል፣ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች በምንኖርበት ኣካባቢ እና በጠቅላላ በዓለም እንዲረጋገጥ ያደርጋል።

መንፈስ ቅዱስ የክርስትያን ነጻነት ማለት መሆኑ በማብራራት እርሱም የእግዚአብሔር መንፈስ የቅድስት ሥላሴ ሶስተኛው አካል፣ በአብ እና በወልድ መካከል ያለው የግኑኝነት አድማስ፣ የስጦታ አድማስ ማለትም በሶስቱ አካል መካከል ያለው የሕይወት ግኑኝነት እና የሚሠዋ ፍቅር የግኑኝነት ተጨባጭ አካል እንደሆነም ገልጠው፣ መንፈስ ቅዱስ መጸለይ ማለት በትህትና መኖር ማለት መሆኑ ገልጠው፣ ይህ ደግሞ ልክ ቅዱስ ጳውሎስ ለገላቲያ ሰዎች በጻፈው መልእክት ምዕራፍ ሁለት ቍ. 20 “እኔ ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀልሁ ያህል ስለምቈጥር ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ እኔ ለራሴ ሕይወት የምኖር አይደለሁም አሁንም በሥጋ የምኖርበት ሕይወት በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን እሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በማመን በተገኘው ሕይወት ነው።” መንፈስ ቅዱስ በኛው ውስጥ ያለ የላቀው ጥበብ መግለጫ መሆኑ እና ይህ በእኛ ውስጥ ያለው ጥበብ፣ ጸጋ እና ጥበብ የሚያሰኘው፣ ከፍጹም እና ከመለኮታዊ ጥበብ ጋር ያለው ሱታፌ እና ከዚህ መለኮታዊ ጥበብ የመነጨ በመሆኑ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ እኛን የዚህ መለኮታዊ ጥበብ ተሳታፊዎች የሚያደርገን ኃይል ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.