2010-05-21 14:02:08

የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት


እ.ኤ.አ. ከ ግንቦት 26 ቀን እስከ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት 19ኛው ይፋዊ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ከምክር ቤቱ የተሰራጨ RealAudioMP3 መግለጫ ያመለክታል።

በዚህ ጉባኤ ብፁዓን ካርዲናላት ብፁዓን አቡናት እና ካህናት በጠቅላላ 23 የምክር ቤቱ አባላት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ 10 የምክር ቤቱ የመማክርት አባላት እንደሚሳተፉም ሲገለጥ፣ ስብሰባው በዚህ በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚታየው የሰዎች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሂደት እግምት ውስት ያስገባ የሚቀርበው ሓዋርያዊ አገልግሎት እና የመንግሥታት እና የአለም አቀፍ ማኅበራት ኃላፊነት በሚል ርእስ ሥር እንደሚመራ ይፋዊ መግለጫ የሰጡት የስደተኞች እና የተጓዦች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በማስታወቅ፣ የስብሰባው መርሃ ግብር በስፋት በማብራራት ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ተራድኦ ማኅበራት እና መንግሥታውያን ያልሆኑት ዓለም አቀፍ የግብረ ሰናይ ማኅበራት ተጠሪዎች እንደሚሳተፉም ገልጠው፣ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ተጋባእያኑ በቅዱስ አባታችን ጋር በመገናኘት እና መሪ ቃል በመቀበል እንደሚጠናቀቅ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.