2010-05-21 14:03:09

ኮንጎ


በኖርድ ኪቩ የሚገኘው የካሪሲምቢ እሳተ ጎመራ በተፋው የቀለጠ ጭቃ መሳይ ፈሻሽ በኪብሪንጋ ክፍል የሆኑት አራት መንደሮችን ሲያወድም፣ 19 ሰዎች የሞት አደጋ እንደደረሰባቸው ሲነገር፣ 27 ሰዎች ገና በመፈለግ RealAudioMP3 ላይ መሆናቸው ተገልጠዋል። ይህ ባለፈው ሳምንት ወደ እሁድ በሚያሸጋግረው ቅዳሜ ሌሊት የተከስተው የተፈጥሮ አደጋ 232 መኖሪያ ቤቶች 205 የእርሻ ክልሎችን እንዳወደመ ሚስና የዜና አገልግሎት በኮንጎ ጎማ ከተማ የሚገኘው ካሪታስ የካቶሊክ የእርዳታ ማኅበር ሠራተኛ ታይለር ቶኤካካላ የሰጡትን መግለጫ በመጥቀስ አስታውቀዋል። የጎማ ሊቀ ጳጳስት ብፁዕ አቡነ ቴኦፊለ ካቦይ ሩቦነካ የሰበካው የክቶሊክ የእርዳታ ድርጅት ቅርንጫፍ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ለተፈናቀሉት 1200 የክልሉ ነዋሪዎች መሠረታዊ የሰብአዊ እርዳታ እያቀረበ መሆኑ ገልጠዋል። የተለያዩ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ማኅበራት የተባበሩት መንግሥታት፣ የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር ልኡካን አደጋው የተከሰተበት ክልል መጎብኘታቸውም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የዚህ ዓይነቱ አደጋ እ.ኤ.አ. በ 1917 እንዲሁም በ 1952 ዓ.ም. ተከስቶ እንደነበርም የዜና አገልግሎት በማስታወስ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.