2010-05-21 13:59:47

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ እውነተኛው ነጻነት እግዚአብሔርን ማወቅ


በጌታ ደስ ይበላችሁ የሚለው ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ለፊሊጲሲዮስ በጻፈው መልእክት ምዕራፍ 4 ቁጥር 10 ያለውን በመጥቀስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በማልታ በወህኒ ቤት ለሚገኙት እስረኞች ባስተላለፉት መልእክት፣ RealAudioMP3 ባለፈው ሚያዝያ ወር ሓዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ የአገሪቱ ሕዝብ ያደረገላቸው አቀባበል መስተንግዶ እንዲሁም እስረኞችን በመጎብኘት ያደረጉት የሀሳስብ ልውውጥ ልባቸውን እንደነካቸውም በመግለጥ እስረኞቹ ላሳዩት ፍቅር እና አክብሮት በማስታወስ፣ በማልታ ወንጌል እንዲገባ እና እንዲስፋፋ ያደረገውም ቅዱስ ጳውሎስ መሆኑ አስታውሰው፣ እውነተኛው ነጻነታችን እግዚአብሔር መሆኑ በማብራራት፣ ስለዚህ ሞትም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን መላእክትም ቢሆኑ ባለሥልጣኖች ቢሆኑ አሁን ያለውም ቢሆን በኋላ የሚመጣውም ቢሆን የሰማይ ኃይሎችም ቢሆኑ ከፍታም ቢሆን ዝቅታም ቢሆን ማንኛው ፍጥረት ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ” ሮሜ ምእራፍ 8 ከቁጥር 38 እስከ 39 በመጥቀስ ለእስረኞች ቅርብ መሆናቸውም በማረጋገጥ ዘወትር በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋችውም በመግለጥ ቡራኬ በማቅረብ ሰላም እና ኃይል ከእግዚአብሔር ያገኙ ዘንድ እንደሚጸልዩ ማረጋገጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.