2010-05-21 13:58:39

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ሃይማኖት ለመግባባት እና ለልማት


በቅድስት መንበር የመንጎሊያ ልኡከ መንግሥት እንዲሆኑ ከመንግሥታቸው የተላኵት ወኪል ሉቭሳንተርሰን ኦርጂል ትላትና የሹመት ደብዳቤአቸውን ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ማቅረባቸው የቅድስት RealAudioMP3 መንበር መገልጫ ይጠቁማል።

ቅዱስ አባታችን የሞንጎሊያ አዲሱ ልኡከ መንግሥት ያቀረቡትን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለው ባሰሙት ንግግር፣ በሞንጎሊያ የዲሞክራሲው ሥርዓት ምሥረታ እና የቅድስት መንበር እና የሞንጎሊያ የጋራው ግኑኝነት ጅማሬ 20 ዓመት ማስቆጠሩ በማስታወስ፣ በሞንጎሊያ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የሚያመለክተው የሃይማኖት ነጻነት የማክበር ውሳኔ ትግባሬው የሚመስገን ነው በማለት፣ በዚህ አጋጣሚም በአገሪቱ ያለው ብርዳማው የአየር ጸባይ ሰለባ የሆኑትን በማሰብ ለሕዝቡ እንደሚጸልዩ በማረጋገጥ፣ ሃይማኖት እና ባህል የመላው ሰው ዘር ጥልቅ መንፈሳዊ ስሜት እና ፍላጎት መሆኑ በማብራራት፣ ይኽ ጥልቅ ፍላጎት በሕዝቦች መካከል ውይይት መደጋገፍ የሚያነቃቃ ለሰላም እና ለተገቢው እድገት መሠረት መሆን እንዳለበት በማሳሰብ፣ ለወንጌል ታማኝ የሆነቸው ቤተ ክርስትያን ለሰብአዊ እድገት በመረባረብ ከመንጎሊያ መንግሥት ጋር በመተባበር የአገሪቱ ሕዝብ ከተጋረጠበት ማኅበራዊ ችግር ለማላቀቅ የሚያግዘውን ሰብአዊ እና ባህላዊ ሕጽነት በማቅረብ ወጣቱ የኅብረትሰቡ ክፍል ለመከባበር እና ለመተባበር እንዲሁም በችግር ላይ ለሚገኙት ትኩረት እንዲያደርግ የሚያስችለው ሕንጸት እንደምታቀርብ አረጋግጠዋል።

ቀጥለው አዲሱ የሞንጎሊያ ልኡከ መንግሥት ኦርጂል የሞንጎሊያ የተፈጥሮ ሃብት ለማኅበራዊ እና ለአገር ጥቅም ለሕንጸት መርሃ ግብሮች ማስፈጸሚያ የአግልግሎት መስጫ ለማስፋፋት ዓላማ እንደሚውል በማረጋገጥ፣ በዚህ አጋጣሚም የሞንጎሊያ መንግሥት እ.ኤ.አ. ጥር 2010 ዓ.ም. ከአገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የሞት ቅጣት የሚፈቅደው አንቀጽ እንዲሰረዝ ማድረጉ እና በተለያዩ የተባበሩት መንግሥታት እቅዶች በመሳተፍም አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጠች መሆኗ ገልጠዋል።

በሞንጎሊያ 650 ካቶሊክ ምእመናን 87 ልኡካነ ወንጌል 4 ቁምስናዎች እንዳሉም ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. በ 1995 ዓ.ም የካቶሊክ ምእመናን ብዛት 14 ብቻ እንደነበር የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.