2010-05-21 14:00:46

ለቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ክብር የቀረበው የሙዚቃ ኮንሰርት


በቫቲካን የሩሲያ ሥነ ባህል እና ሥነ ሃይማኖት እለት ለሁለት ቀን በተለያዩ ዓውደ ጥናቶች እና በጋራ ውይይቶች ተሸኝቶ መታሰቡ ሲገለጥ፣ ዕለቱ ትላትና ቫቲካን በሚገኘው በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ፣ RealAudioMP3 የሞስኮ እና የመላ ሩሲያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አንደኛ ለቅዱስ አባታችን ክብር በሩሲያ ብሔራዊ ሙዚቀኞች አማካኝነት በካርሎ ፕኖንቲ ዩኒይር በተመራው የሙዚቃ ኮንሰርት አማካኝነት መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የሙዚቃው ኮንሰርት ከመቅረቡም ቀደም በማድረግ ለሩሲያ ፓትሪያርክ የውጭ ጉኑኝነት ተጠሪ ሜትሮፖሊታ ሂላሪዮን አልፈየቭ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አንደኛ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት መነበቡም ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሙዚቃው ኮንሰርት እንዳበቃም ንግግር ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.