2010-05-20 14:07:51

የተፈጥሮ ሃብት በትክክል መጠቀም


የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ብፁዓን ጳጳሳታ ምክር ቤት፣ ይህች በተፈጥሮ ሃብት የታደለቸው አገራቸው ያላት የተፈጥሮ ሃብት የመጠቀሙ ሂደት በሥነ ምግባር የተካነ ይሆን ዘንድ አሳስብዋል። RealAudioMP3

ብፁዓን ጳጳሳት የተፈጥሮ ሃብት ጸጋ መሆኑም በማብራራት፣ ለአገር እና ለህዝብ ጥቅም መዋል አለበት እንጂ ለጥቂቱ ሃብት ማደለቢያ መሆን የለበትም ብለዋል። የአገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት ለግጭት ለውጥረት እና ለተገዥነት አደጋ እያጋለጠ መሆኑ እግምት ውስጥ በማስገባት የኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. የተፈጥሮ ሃብት ጉዳይ የሚከታተል ጳጳሳዊ ድርገት ማቋቋሙ ሚስና የዜና አገግሎት በማስታወስ፣ የተፈጥሮ ሃብት የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት ለጥቅም እንዲውል በማጣራት ለምርት የሚያቀርቡት ኅብረ ኢንዳስትሪዎች የግል ሃብት ከማካበት ፈተና ተላቀው የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ልማት ማነቃቃት እና ለአገሪቱ እድገት ደጋፍያን መሆን እንደሚጠበቅባቸው በማሳሰብ ይህ ደግሞ ኃላፊነትም ጭምር ነው እንዳለም የዜና አገልግሎቱ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.