2010-05-20 14:10:06

የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪቃ ኅብረት


እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. የአፍሪካ የኤኮኖሚ እድገት አመርቂ መሆኑ የአፍሪቃ ጉዳይ የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤት እና የአፍሪቃ ኅብረት የአፍሪቃ የኤኮኖሚ ሂደት በማስመለከት ያሠራጩት የጥናት ሰነድ የጠቀሰው ሚስና RealAudioMP3 የዜና አገልግሎት አስታወቀ። የ 2010 ዓ.ም. የአፍሪቃ ኤኮኖሚ እድገት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 4.8% ከፍ ማለቱ እና ይህ ደግሞ የአፍሪቃ ኤኮኖሚ የምርት አቅርቦት ብቃት ከፍ እንደሚያደርገው ሲረጋገጥ፣ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ያስከተለው የኤክኖሚ ግሽበት መሻሻል እያሳየ በመሆኑም ይህ ሂደት የአፍሪቃ የምርት አቅርቦት እንደሚያበረታታ ሚስና የዜና አገልግሎት ሰነዱን በማስደገፍ ያሰራጨው ዜና ያረጋገጣል።

በክልል አንጻርም ሲታይ ሰሜን አፍሪቃ በ 6.4% ምስራቅ አፍሪቃ በ 5.4% የአፍሪቃው ድቡባዊው ክልል በ 3.8% እድገት ማሳይቱ እና እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. የአፍሪቃው የኤክኖሚው እድገት ያለው የኤኮኖሚ እድገት ሁኔታ በማስደገፍ በግምት 5.9% እንደሚለካ ሰነዱ ከወዲሁ እንዳብራራም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.